وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا مَا كُنتَ تَدْرِى مَا ٱلْكِتَٰبُ وَلَا ٱلْإِيمَٰنُ وَلَٰكِن جَعَلْنَٰهُ نُورًا نَّهْدِى بِهِۦ مَن نَّشَآءُ مِنْ عِبَادِنَا وَإِنَّكَ لَتَهْدِىٓ إِلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ
Amharic Translation - Africa Academy52. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ልክ እንደዚሁ ወደ አንተ ከትዕዛዛችን ሲሆን ሂወት የሆነውን (ቁርአን) አወረድነው:: መጽሐፉም ሆነ እምነቱ ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም:: ግን ቁርኣንን ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው:: አንተም ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲኾን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደኾነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡ አንተ ወደ ቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ትመራለህ፡፡