caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Muhammad፣ አንቀጽ 15

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 95 · 47:15

مَّثَلُ ٱلْجَنَّةِ ٱلَّتِى وُعِدَ ٱلْمُتَّقُونَ فِيهَآ أَنْهَٰرٌ مِّن مَّآءٍ غَيْرِ ءَاسِنٍ وَأَنْهَٰرٌ مِّن لَّبَنٍ لَّمْ يَتَغَيَّرْ طَعْمُهُۥ وَأَنْهَٰرٌ مِّنْ خَمْرٍ لَّذَّةٍ لِّلشَّٰرِبِينَ وَأَنْهَٰرٌ مِّنْ عَسَلٍ مُّصَفًّى وَلَهُمْ فِيهَا مِن كُلِّ ٱلثَّمَرَٰتِ وَمَغْفِرَةٌ مِّن رَّبِّهِمْ كَمَنْ هُوَ خَٰلِدٌ فِى ٱلنَّارِ وَسُقُوا۟ مَآءً حَمِيمًا فَقَطَّعَ أَمْعَآءَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy15. ያች አላህን ለሚፈሩ ሰዎች ቃል የተገባችው ገነት (ይህን ትመስላለች)፤ በውስጧ ሽታው ከማይለወጥ የውሃ ወንዞች፤ ጣዕሙ የማይለወጥ የወተት ወንዞች፤ ለጠጪዎች ሁሉ እጅግ ጣፋጭ የሆኑ የወይን ጠጅ ወንዞችና የንጹህ(የተነጠረ) ማር ወንዞች አሉባት:: በውስጧ ሁሉም የፍራፍሬ አይነቶች ከጌታቸዉም ምህረት ተዘጋጅተውላቸዋል:: በእነዚህ ገነቶች የሆነ እንደነዚያ እሳት ውስጥ ዘወትር እንደሚኖሩ የፈላ ውሃም እንዲጠጡ እንደሚደረጉትና ውሃዉም የሆድ ዕቃቸውን እንደሚበጣጥስባቸው ነውን? አይደለም።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየዚያች ጥንቁቆቹ ተስፋ የተሰጧት ገነት ምስል በውስጧ ሺታው ከማይለወጥ ውሃ ወንዞች፣ ጣዕሙ ከማይለወጥ ወተትም ወንዞች፣ ለጠጪዎች ሁሉ ጣፋጭ ከኾነች የወይን ጠጅም ወንዞች ከተነጠረ ማርም ወንዞች አልሉባት፡፡ ለእነርሱም በውስጧ ከፍሬዎች ሁሉ (በያይነቱ) ከጌታቸው ምሕረትም አልላቸው፡፡ (በዚች ገነት ውስጥ ዘውታሪ የኾነ ሰው) እርሱ በእሳት ውስጥ ዘውታሪ እንደኾነ ሰው፣ ሞቃትንም ውሃ እንደተጋቱ፣ አንጀቶቻቸውንም ወዲያውኑ እንደቆራረጠው ነውን? (አይደለም)፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70