caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Muhammad፣ አንቀጽ 20

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 95 · 47:20

وَيَقُولُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَوْلَا نُزِّلَتْ سُورَةٌ فَإِذَآ أُنزِلَتْ سُورَةٌ مُّحْكَمَةٌ وَذُكِرَ فِيهَا ٱلْقِتَالُ رَأَيْتَ ٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ يَنظُرُونَ إِلَيْكَ نَظَرَ ٱلْمَغْشِىِّ عَلَيْهِ مِنَ ٱلْمَوْتِ فَأَوْلَىٰ لَهُمْ

Amharic Translation - Africa Academy20. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ያመኑት ሰዎች (ለዲን ለመታገል ግፊት ያለበት)« የቁርኣን ምዕራፍ አይወረድም ኖሯልን?» ይላሉ:: የጠነከረም ምዕራፍ በወረደና በውስጡም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ የንፍቅና በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የሆነ መከራ በእርሱ ላይ እንደወደቀበት ሰው አስተያያት ወደ አንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ:: ለእነርሱው ተገባቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም ያመኑት ሰዎች (መታገል ያለባት) «ሱራ አትወርድም ኖሮአልን?» ይላሉ፡፡ የጠነከረችም ሱራ በተወረደችና በውስጧም መጋደል በተወሳ ጊዜ እነዚያን በልቦቻቸው ውስጥ (የንፍቅና) በሺታ ያለባቸውን ሰዎች ከሞት የኾነ መከራ በርሱ ላይ እንደ ወደቀበት ሰው አስተያየት ወዳንተ ሲመለከቱ ታያቸዋለህ፡፡ ለእነሱም ወዮላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70