caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Fath الفتح

29 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 111

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِنَّا فَتَحْنَا لَكَ فَتْحًا مُّبِينًا

Amharic Translation - Africa Academy1. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ ላንተ (መካን) በመክፈት ግልጽ የሆነን ድል ለገስንህ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّيَغْفِرَ لَكَ ٱللَّهُ مَا تَقَدَّمَ مِن ذَنۢبِكَ وَمَا تَأَخَّرَ وَيُتِمَّ نِعْمَتَهُۥ عَلَيْكَ وَيَهْدِيَكَ صِرَٰطًا مُّسْتَقِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy2. አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን ኃጢአትክን ሊምርህ፤ ፀጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላና ቀጥተኛዉን መንገድ ሊመራህ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَنصُرَكَ ٱللَّهُ نَصْرًا عَزِيزًا

Amharic Translation - Africa Academy3. አላህም ብርቱን እርዳታ ሊረዳህ መካን ከፈተልህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِىٓ أَنزَلَ ٱلسَّكِينَةَ فِى قُلُوبِ ٱلْمُؤْمِنِينَ لِيَزْدَادُوٓا۟ إِيمَٰنًا مَّعَ إِيمَٰنِهِمْ وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَكَانَ ٱللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy4. አላህ ያ በአማኞች ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው:: አላህ የሰማይና የምድር ስራዊት ሁሉ የሱ ብቻ ነው:: አላህ ሁሉን አዋቂና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّيُدْخِلَ ٱلْمُؤْمِنِينَ وَٱلْمُؤْمِنَٰتِ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا وَيُكَفِّرَ عَنْهُمْ سَيِّـَٔاتِهِمْ وَكَانَ ذَٰلِكَ عِندَ ٱللَّهِ فَوْزًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy5. ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናትን በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ሊያስገባቸው፤ ከነርሱም ሐጢያቶቻቸዉን ሊያብስላቸው (መካን ከፈተልህ):: ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ መታደል ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيُعَذِّبَ ٱلْمُنَٰفِقِينَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتِ وَٱلْمُشْرِكِينَ وَٱلْمُشْرِكَٰتِ ٱلظَّآنِّينَ بِٱللَّهِ ظَنَّ ٱلسَّوْءِ عَلَيْهِمْ دَآئِرَةُ ٱلسَّوْءِ وَغَضِبَ ٱللَّهُ عَلَيْهِمْ وَلَعَنَهُمْ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَهَنَّمَ وَسَآءَتْ مَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy6. በአላህም ክፉ ጥርጣሬን ወንድ ተጣራጣሪ አስመሳዮችንና ሴት አስመሳዮችን ወንድ አጋሪዎችና ሴት አጋሪዎችን ያሰቃይም ዘንድ (በትግል አዘዘ):: በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው:: በእነርሱ ላይ አላህ ተቆጣባቸው ረገማቸዉም:: ለእነርሱ ገሀነምን አዘጋጀላቸው:: ገሀነም መመለሻነቷም ከፋች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ جُنُودُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy7. ለአላህ የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አሉት:: አላህ ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّآ أَرْسَلْنَٰكَ شَٰهِدًا وَمُبَشِّرًا وَنَذِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy8. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እኛ መስካሪ፤ አብሳሪና አስፈራሪ አድርገን በእርግጥ ላክንህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِّتُؤْمِنُوا۟ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتُعَزِّرُوهُ وَتُوَقِّرُوهُ وَتُسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy9. በአላህ ልታምኑ። በመልዕክተኛዉም ልታምኑ፤ ልትረዱትና ልታከብሩት፤ አላህንም በጠዋትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱት (ላክንህ)።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ يُبَايِعُونَكَ إِنَّمَا يُبَايِعُونَ ٱللَّهَ يَدُ ٱللَّهِ فَوْقَ أَيْدِيهِمْ فَمَن نَّكَثَ فَإِنَّمَا يَنكُثُ عَلَىٰ نَفْسِهِۦ وَمَنْ أَوْفَىٰ بِمَا عَٰهَدَ عَلَيْهُ ٱللَّهَ فَسَيُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው:: የአላህ እጅ ከእጆቻቸው በላይ ነው:: ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው:: በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላ ሰው ታላቅ ምንዳ በእርግጥ ይሰጠዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيَقُولُ لَكَ ٱلْمُخَلَّفُونَ مِنَ ٱلْأَعْرَابِ شَغَلَتْنَآ أَمْوَٰلُنَا وَأَهْلُونَا فَٱسْتَغْفِرْ لَنَا يَقُولُونَ بِأَلْسِنَتِهِم مَّا لَيْسَ فِى قُلُوبِهِمْ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ لَكُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا إِنْ أَرَادَ بِكُمْ ضَرًّا أَوْ أَرَادَ بِكُمْ نَفْعًۢا بَلْ كَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًۢا

Amharic Translation - Africa Academy11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዐረብ ዘላኖች መካከል እነዚያ ከዘመቻ ወደ ኋላ የቀሩት «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸግረዉን ስለነበር ነውና (የቀረነው) ምህረትን ለምንልን» ይሉሃል:: በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ:: «አላህ እናንተን መጉዳትም ሆነ መጥቀም ቢፈልግ ከአላህ ለእናተ አንዳችን ለመከላከል የሚችል ማን ነው? በእውነቱ አላህ ለምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

بَلْ ظَنَنتُمْ أَن لَّن يَنقَلِبَ ٱلرَّسُولُ وَٱلْمُؤْمِنُونَ إِلَىٰٓ أَهْلِيهِمْ أَبَدًا وَزُيِّنَ ذَٰلِكَ فِى قُلُوبِكُمْ وَظَنَنتُمْ ظَنَّ ٱلسَّوْءِ وَكُنتُمْ قَوْمًۢا بُورًا

Amharic Translation - Africa Academy12. ይልቁንም መልዕክተኛውና ምዕመናኖቹ ወደየቤተሰቦቻቸው ፈጽሞ አለመመለሳቸውን እርግጠኞች (ተጠራጣሪዎች) ስለነበራችሁ ነው። ይህም በልቦቻችሁ ውስጥ ተሸለመላችሁ:: መጥፎንም መጠርጠር ጠረጠራችሁ ጠፊዎች ህዝቦችም ሆናችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَن لَّمْ يُؤْمِنۢ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ فَإِنَّآ أَعْتَدْنَا لِلْكَٰفِرِينَ سَعِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy13. በአላህና በመልዕክተኛው ላለመነ ሰው እኛ ለከሓዲያን እሳትን አዘጋጅተናል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلِلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ يَغْفِرُ لِمَن يَشَآءُ وَيُعَذِّبُ مَن يَشَآءُ وَكَانَ ٱللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy14. የሰማያትና የምድር ንግስና የአላህ ብቻ ነው:: የሚፈልገውን ወደ ቀናው ይመራል:: የሚፈልገውንም ሰው ይቀጣል:: አላህ መሀሪና አዛኝ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَيَقُولُ ٱلْمُخَلَّفُونَ إِذَا ٱنطَلَقْتُمْ إِلَىٰ مَغَانِمَ لِتَأْخُذُوهَا ذَرُونَا نَتَّبِعْكُمْ يُرِيدُونَ أَن يُبَدِّلُوا۟ كَلَٰمَ ٱللَّهِ قُل لَّن تَتَّبِعُونَا كَذَٰلِكُمْ قَالَ ٱللَّهُ مِن قَبْلُ فَسَيَقُولُونَ بَلْ تَحْسُدُونَنَا بَلْ كَانُوا۟ لَا يَفْقَهُونَ إِلَّا قَلِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy15. ከጠላት የተማረኩትን ገንዘቦች ልትይዙ በሄዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች «ተውን እንከተላችሁ» ይሏችኋል:: በዚህም የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ:: «ፈጽሞ አትከተሉንም:: ልክ እንደዚሃችሁ ቃል የመሰለ ከዚህ በፊት አላህም ብሏል» በሏቸው:: «ይልቁንም ትመቀኙናላችሁ» ይላሉም:: በእውነት እነርሱም ጥቂትን እንጂ የማያውቁ ነበሩ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

قُل لِّلْمُخَلَّفِينَ مِنَ ٱلْأَعْرَابِ سَتُدْعَوْنَ إِلَىٰ قَوْمٍ أُو۟لِى بَأْسٍ شَدِيدٍ تُقَٰتِلُونَهُمْ أَوْ يُسْلِمُونَ فَإِن تُطِيعُوا۟ يُؤْتِكُمُ ٱللَّهُ أَجْرًا حَسَنًا وَإِن تَتَوَلَّوْا۟ كَمَا تَوَلَّيْتُم مِّن قَبْلُ يُعَذِّبْكُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy16. ዘላኖች (ከአዕራቦች) ወደ ኋላ ለቀሩት (እንዲህ) በላቸው: «የብርቱ ጭካኔ ባለቤት ወደ ሆኑ ህዝቦች ውጊያ ወደ ፊት ትጠራላችሁ፤ ትጋደሏቸዋላችሁ:: ወይም ይሰልማሉ ብትታዘዙም አላህ መልካም ምንዳን ይሰጣችኋል:: ከአሁን በፊት እንደ ሸሻችሁ ብትሸሹ ደግሞ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣችኋል::»

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّيْسَ عَلَى ٱلْأَعْمَىٰ حَرَجٌ وَلَا عَلَى ٱلْأَعْرَجِ حَرَجٌ وَلَا عَلَى ٱلْمَرِيضِ حَرَجٌ وَمَن يُطِعِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ يُدْخِلْهُ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ وَمَن يَتَوَلَّ يُعَذِّبْهُ عَذَابًا أَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy17. (ሰዎች ሆይ!) በአይነስውር ላይ (ከዘመቻ በመቅረቱ) ኃጢአት የለበትም:: በአንካሳ ላይም ኃጢአት የለበትም:: በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም:: አላህንና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሁሉ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያስገባዋል:: የሚያፈገፍገዉንም ሁሉ አሳማሚ ቅጣት ይቀጣዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّقَدْ رَضِىَ ٱللَّهُ عَنِ ٱلْمُؤْمِنِينَ إِذْ يُبَايِعُونَكَ تَحْتَ ٱلشَّجَرَةِ فَعَلِمَ مَا فِى قُلُوبِهِمْ فَأَنزَلَ ٱلسَّكِينَةَ عَلَيْهِمْ وَأَثَٰبَهُمْ فَتْحًا قَرِيبًا

Amharic Translation - Africa Academy18. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከምዕመናኖቹ በዛፊቱ ስር ቃል ኪዳን በሚጋቡህ ጊዜ አላህ በእርግጥ ስራቸዉን ወደደላቸው:: በልቦቻቸዉም ውስጥ ያለውን ዐወቀ:: በነሱም ላይ እርጋታን አወረደ:: ቅርብ የሆነንም መክፈት መነዳቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَغَانِمَ كَثِيرَةً يَأْخُذُونَهَا وَكَانَ ٱللَّهُ عَزِيزًا حَكِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy19. ብዙዎች የተማረኩትን ገንዘቦች የሚወስዷቸው የሆኑን መነዳቸው:: አላህም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَعَدَكُمُ ٱللَّهُ مَغَانِمَ كَثِيرَةً تَأْخُذُونَهَا فَعَجَّلَ لَكُمْ هَٰذِهِۦ وَكَفَّ أَيْدِىَ ٱلنَّاسِ عَنكُمْ وَلِتَكُونَ ءَايَةً لِّلْمُؤْمِنِينَ وَيَهْدِيَكُمْ صِرَٰطًا مُّسْتَقِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy20. (አማኞች ሆይ!) አላህ ብዙዎቹን ምርኮዎች የምትወስዷቸው የሆኑን አላህ ቃል ገባላችሁ። ይህንንም ለእናንተ አስቸኮለላቻችሁ:: ከናንተም የሰዎችን እጆች ሠበሰበላችሁ። ብታመሰግኑና ለአማኞችም መልዕክት እንድትሆን ቀጥተኛውን መንገድ ይመራችሁም ዘንድ ይህን አደረግንላችሁ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأُخْرَىٰ لَمْ تَقْدِرُوا۟ عَلَيْهَا قَدْ أَحَاطَ ٱللَّهُ بِهَا وَكَانَ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy21. ሌላይቱንም በእርሷ ላይ ገና ያልቻላችኋትን አላህ ያወቃትን ለእናንተ አዘጋጅቷል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْ قَٰتَلَكُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَوَلَّوُا۟ ٱلْأَدْبَٰرَ ثُمَّ لَا يَجِدُونَ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy22. እነዚያም የካዱት (የመካ ሰዎች) በተዋጓችሁ ኖሮ ለሽሽት ጀርባዎችን ባዞሩ ነበር:: ከዚያ ዘመድም ረዳትም አያገኙም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سُنَّةَ ٱللَّهِ ٱلَّتِى قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلُ وَلَن تَجِدَ لِسُنَّةِ ٱللَّهِ تَبْدِيلًا

Amharic Translation - Africa Academy23. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ያችን ከዚህ በፊት በእርግጥ ያለችፈውን ልማድ ደነገገ:: ለአላህ ልማድ መቸም ለውጥን አታገኝም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَهُوَ ٱلَّذِى كَفَّ أَيْدِيَهُمْ عَنكُمْ وَأَيْدِيَكُمْ عَنْهُم بِبَطْنِ مَكَّةَ مِنۢ بَعْدِ أَنْ أَظْفَرَكُمْ عَلَيْهِمْ وَكَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرًا

Amharic Translation - Africa Academy24. እርሱ(አላህ) ያ በመካ ውስጥ በእነርሱ ላይ ካስቻላችሁ በኋላ እጆቻቸዉን ከእናንተ ላይ እጆቻችሁንም ከእነርሱ ላይ የከለከለ ነው:: አላህም የምትሰሩትን ነገር ሁሉ ተመልካች ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَصَدُّوكُمْ عَنِ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَٱلْهَدْىَ مَعْكُوفًا أَن يَبْلُغَ مَحِلَّهُۥ وَلَوْلَا رِجَالٌ مُّؤْمِنُونَ وَنِسَآءٌ مُّؤْمِنَٰتٌ لَّمْ تَعْلَمُوهُمْ أَن تَطَـُٔوهُمْ فَتُصِيبَكُم مِّنْهُم مَّعَرَّةٌۢ بِغَيْرِ عِلْمٍ لِّيُدْخِلَ ٱللَّهُ فِى رَحْمَتِهِۦ مَن يَشَآءُ لَوْ تَزَيَّلُوا۟ لَعَذَّبْنَا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy25. እነርሱ ማለት እነዚያ በአላህ የካዱ፤ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ መስዋዕትንም የታሰረ ሲሆን ወደ ስፍራው እንዳይደርስ የከለከሉ ናቸው:: የማታውቋቸው ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናት ከከሓዲያኑ ጋር ባልነበሩ ኖሮና እናንተም ያለ እውቀት እነርሱን ረግጣችሁ ከእነርሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባይሆን ኖሮ እጆቻችሁን ባላገድን ነበር:: አላህም የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባ ዘንድ (እጆቻችሁን አገደ):: በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእርሱ ውስጥ በአላህ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِذْ جَعَلَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فِى قُلُوبِهِمُ ٱلْحَمِيَّةَ حَمِيَّةَ ٱلْجَٰهِلِيَّةِ فَأَنزَلَ ٱللَّهُ سَكِينَتَهُۥ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ وَعَلَى ٱلْمُؤْمِنِينَ وَأَلْزَمَهُمْ كَلِمَةَ ٱلتَّقْوَىٰ وَكَانُوٓا۟ أَحَقَّ بِهَا وَأَهْلَهَا وَكَانَ ٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمًا

Amharic Translation - Africa Academy26. እነዚያን በአላህ የካዱት ደራይቱን (እልህን) የመሀይምነቲቱን ደራ (እልህ) በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ በቀጣናቸው ነበር:: አላህም በመልዕክተኛው ላይ እና በምዕመናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ:: መጠበቂያይቱንም ቃል አስያዛቸው:: በእርሷም ተገቢዎች ባለቤቶቿም ነበሩ:: አላህም በነገሩ ሁሉ አዋቂ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَّقَدْ صَدَقَ ٱللَّهُ رَسُولَهُ ٱلرُّءْيَا بِٱلْحَقِّ لَتَدْخُلُنَّ ٱلْمَسْجِدَ ٱلْحَرَامَ إِن شَآءَ ٱللَّهُ ءَامِنِينَ مُحَلِّقِينَ رُءُوسَكُمْ وَمُقَصِّرِينَ لَا تَخَافُونَ فَعَلِمَ مَا لَمْ تَعْلَمُوا۟ فَجَعَلَ مِن دُونِ ذَٰلِكَ فَتْحًا قَرِيبًا

Amharic Translation - Africa Academy27. ህልሙ እውነተኛ ሲሆን አላህ የፈለገ አንደሆነ ጸጥተኞች ሆናችሁ ራሳችሁን ላጭታችሁ አሳጥራችሁ የማትፈሩ ስትሆኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ ያለውን ህልም አሏህ ለመልዕክተኛው(ለሙሀመድ) እውነት አደረገለት:: አላህ (ከእርቁ) ከመመለሳችሁ ሂደት ያላወቃችሁትንም ነገር አወቀ:: እናም ከዚህ በፊት ቅርብን የመክፈት እርቅ አደረገ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ شَهِيدًا

Amharic Translation - Africa Academy28. እርሱ (አላህ) ያ መልዕክተኛውን (ነብዩ ሙሐመድን) በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሀይማኖት በሁሉ ላይ ሊያልቀው (የበላይ ሊያደርገው) የላከ ነው:: መስካሪነትም አላህ በቃ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥٓ أَشِدَّآءُ عَلَى ٱلْكُفَّارِ رُحَمَآءُ بَيْنَهُمْ تَرَىٰهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضْوَٰنًا سِيمَاهُمْ فِى وُجُوهِهِم مِّنْ أَثَرِ ٱلسُّجُودِ ذَٰلِكَ مَثَلُهُمْ فِى ٱلتَّوْرَىٰةِ وَمَثَلُهُمْ فِى ٱلْإِنجِيلِ كَزَرْعٍ أَخْرَجَ شَطْـَٔهُۥ فَـَٔازَرَهُۥ فَٱسْتَغْلَظَ فَٱسْتَوَىٰ عَلَىٰ سُوقِهِۦ يُعْجِبُ ٱلزُّرَّاعَ لِيَغِيظَ بِهِمُ ٱلْكُفَّارَ وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِنْهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًۢا

Amharic Translation - Africa Academy29. የአላህ መልዕክተኛ (ነብዩ) ሙሐመድ እና እነዚያም የእርሱ ጓደኞች በከሓዲያን ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው ተዛዛኞች ናቸው:: አጎንባሾች፤ ሰጋጆች፤ ሆነው ታያቸዋልህ:: ችሮታንና ውዴታን ሁልጊዜም ከአላህ ይፈልጋሉ:: ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትሆን በፊታቸው ላይ ናት:: ይህ በተውራት (የተነገረላቸው) ጸባያቸው ነው:: በኢንጅል ውስጥ የተጠቀሰው ምሳሌያቸው ደግሞ ቀንዘሉን እንደ አወጣ አዝመራና (ቀንዘሉን) እንዳበረታው እንደ ወፍራምና ገበሬዎቹን የሚያስደነቅ ሆኖ አገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደቆመ (አዝመራ) ነው:: ያበረታቸውና ከሓዲያን በእርሱ ሊያሰቆጭ ነው:: አላህ እነዚያን በእሱ ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን ተግባራት የሰሩትን ሁሉ ምህረትንና ታላቅ ምንዳን ቃል ገበቶላቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70