caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Anbiyaa፣ አንቀጽ 87

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 73 · 21:87

وَذَا ٱلنُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَٰضِبًا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقْدِرَ عَلَيْهِ فَنَادَىٰ فِى ٱلظُّلُمَٰتِ أَن لَّآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنتَ سُبْحَٰنَكَ إِنِّى كُنتُ مِنَ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy87. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በሄደ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መሆናችንን ጠረጠረ:: ዓሳም ዋጠው:: በጨለማዎችም ውስጥ ሆኖ «ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም ጥራት ይገባህ:: እኔ በእርግጥ ከበዳዮች ነበርኩ።» በማለት ተጣራ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ (ዓሳም ዋጠው)፡፡ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70