caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Bayyina البينة

8 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 100

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ لَمْ يَكُنِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ وَٱلْمُشْرِكِينَ مُنفَكِّينَ حَتَّىٰ تَأْتِيَهُمُ ٱلْبَيِّنَةُ

Amharic Translation - Africa Academy1. ከመጽሐፍ ባለቤቶችና ከአጋሪዎች እነዚያ በአላህ የካዱት ሰዎች ግልጽ አስረጂ እስኪመጣላቸው ድረስ (ከነበሩበት አቋም) ተወጋጆች አልነበሩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَسُولٌ مِّنَ ٱللَّهِ يَتْلُوا۟ صُحُفًا مُّطَهَّرَةً

Amharic Translation - Africa Academy2. (አስረጂውም) የተጥራሩ (መጽሐፎችን) የሚያነብ ከአላህ የሆነ መልዕክተኛ ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فِيهَا كُتُبٌ قَيِّمَةٌ

Amharic Translation - Africa Academy3. በውስጧም ቀጥተኛ የሆኑ ጹሁፎች ያሉባት የሆነችን (አስረጂ)፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَا تَفَرَّقَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَتْهُمُ ٱلْبَيِّنَةُ

Amharic Translation - Africa Academy4. እነዚያ መጽሐፉን የተሰጡ ሰዎችም ግልጽ አስረጂ ከመጣላቸው በኋላ እንጂ አልተለያዩም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أُمِرُوٓا۟ إِلَّا لِيَعْبُدُوا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ حُنَفَآءَ وَيُقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَيُؤْتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَذَٰلِكَ دِينُ ٱلْقَيِّمَةِ

Amharic Translation - Africa Academy5. ሃይማኖትን ለአላህ ብቻ አጥሪዎችና ቀጥተኞች ሆነው አላህን ሊገዙት፤ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፤ ዘካንም በትክክል ሊሰጡ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆን ተለያዩ:: የቀጥተኛይቱ ሃይማኖት ድንጋጌም ይሀው ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ وَٱلْمُشْرِكِينَ فِى نَارِ جَهَنَّمَ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمْ شَرُّ ٱلْبَرِيَّةِ

Amharic Translation - Africa Academy6. ከመጽሐፉ ባለቤቶችና ከአጋሪዎች እነዚያ የካዱት በውስጧ ዘውታሪዎች በሚሆኑባት የገሀነም እሳት ውስጥ ናቸው:: እነዚያ ከፍጥረቱ ሁሉ መጥፎዎቹ እነርሱ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمْ خَيْرُ ٱلْبَرِيَّةِ

Amharic Translation - Africa Academy7. እነዚያ በትክክል አምነው በጎ ተግባራትንም የሰሩት እነዚያ ከፍጥረት ሁሉ በላጭ (ምርጦች) የሆኑት እነርሱ ናቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

جَزَآؤُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّٰتُ عَدْنٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا رَّضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا۟ عَنْهُ ذَٰلِكَ لِمَنْ خَشِىَ رَبَّهُۥ

Amharic Translation - Africa Academy8. ምንዳቸውም በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ከጌታቸው ዘንድ የሚቸሯቸው የመኖሪያ ገነቶች ናቸው። በውስጣቸው ለዘልዓለም ዘወታሪዎች ሲሆኑ ይገቡባቸዋል:: አላህ ከእነርሱ ስራቸውን ወደደላቸው:: እነርሱም ከእርሱ ምንዳውን ወደዱ:: ይህ እድል ጌታውን ለፈራ ሁሉ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70