جَزَآؤُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ جَنَّٰتُ عَدْنٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا رَّضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا۟ عَنْهُ ذَٰلِكَ لِمَنْ خَشِىَ رَبَّهُۥ
Amharic Translation - Africa Academy8. ምንዳቸውም በስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ከጌታቸው ዘንድ የሚቸሯቸው የመኖሪያ ገነቶች ናቸው። በውስጣቸው ለዘልዓለም ዘወታሪዎች ሲሆኑ ይገቡባቸዋል:: አላህ ከእነርሱ ስራቸውን ወደደላቸው:: እነርሱም ከእርሱ ምንዳውን ወደዱ:: ይህ እድል ጌታውን ለፈራ ሁሉ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የመኖሪያ ገነቶች ነው፡፡ በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ (ይገቡባቸወል)፡፡ አላህ ከእነርሱ ወደደ፡፡ ከእርሱም ወደዱ፡፡ ይህ ጌታውን ለፈራ ሰው ነው፡፡