caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Hashr الحشر

24 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 101

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy1. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ አላህን አጠራ:: እርሱም ሁሉንም አሸናፊና ጥበበኛው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِىٓ أَخْرَجَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ مِن دِيَٰرِهِمْ لِأَوَّلِ ٱلْحَشْرِ مَا ظَنَنتُمْ أَن يَخْرُجُوا۟ وَظَنُّوٓا۟ أَنَّهُم مَّانِعَتُهُمْ حُصُونُهُم مِّنَ ٱللَّهِ فَأَتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِنْ حَيْثُ لَمْ يَحْتَسِبُوا۟ وَقَذَفَ فِى قُلُوبِهِمُ ٱلرُّعْبَ يُخْرِبُونَ بُيُوتَهُم بِأَيْدِيهِمْ وَأَيْدِى ٱلْمُؤْمِنِينَ فَٱعْتَبِرُوا۟ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَبْصَٰرِ

Amharic Translation - Africa Academy2. እርሱ ያ! ከመጽሐፍ ሰዎች መካከል እነዚያን በአላህ የካዱትን ወገኖች ከቤቶቻቸው የመጀመሪያውን ማስወጣት ያስወጣቸው ነው:: (ሙስሊሞች ሆይ!) መውጣታቸውንም አላሰባችሁትም ነበር:: እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ ኃይል የሚከላከሉላቸው መሆናቸውን አሰቡ:: አላህ ግን ካላሰቡት በኩል መጣባቸው:: እናም በልቦቻቸው ውስጥ መርበድበድን (ፍርሃትን) ጣለባቸው:: ቤቶቻቸውን በገዛ እጆቻቸውና በትክክለኛ አማኞች እጅ ያፈርሳሉ (አፈረሱ):: እናንተ የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! አስተውሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَوْلَآ أَن كَتَبَ ٱللَّهُ عَلَيْهِمُ ٱلْجَلَآءَ لَعَذَّبَهُمْ فِى ٱلدُّنْيَا وَلَهُمْ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ عَذَابُ ٱلنَّارِ

Amharic Translation - Africa Academy3. በእነርሱም ላይ አላህ ከአገር መውጣትን ባልፈረደ ኖሮ በቅርቢቱ ዓለም በቀጣቸው ነበር:: ለእነርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም የእሳት ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ شَآقُّوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَمَن يُشَآقِّ ٱللَّهَ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy4. ይህ እነርሱ አላህንና መልዕክተኛውን በመከራከራቸው ምክንያት ነው:: አላህን የሚከራከር ሰው ሁሉ (ይቀጣዋል።) አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና ይቀጣቸዋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَا قَطَعْتُم مِّن لِّينَةٍ أَوْ تَرَكْتُمُوهَا قَآئِمَةً عَلَىٰٓ أُصُولِهَا فَبِإِذْنِ ٱللَّهِ وَلِيُخْزِىَ ٱلْفَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy5. ከዘንባባ (ከተምር ዛፍ) ማንኛዋም የቆረጣችኋት ወይም በግንዶቿ ላይ የቆመች ሆና የተዋችኋት ሁሉ በአላህ ፈቃድ ነው:: አመጸኞችንም ያዋርድ ዘንድ (መቁረጥን ፈቀደ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ مِنْهُمْ فَمَآ أَوْجَفْتُمْ عَلَيْهِ مِنْ خَيْلٍ وَلَا رِكَابٍ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ يُسَلِّطُ رُسُلَهُۥ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy6. ከእነርሱም ገንዘብ ወደ መልዕክተኛው አላህ የመለሰውን በእርሱ ላይ ፈረሶችንና ግመሎችን አላስጋልባችሁበትም:: ግን አላህ መልዕክተኞቹን በሚሻው ላይ ይሾማል:: አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

مَّآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ مِنْ أَهْلِ ٱلْقُرَىٰ فَلِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ كَىْ لَا يَكُونَ دُولَةًۢ بَيْنَ ٱلْأَغْنِيَآءِ مِنكُمْ وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy7. አላህ ከከተሞች ሰዎች ሀብት መካከል በመልዕክተኛው ላይ የመለሰው ሀብት ከናንተ ውስጥ በሀብታሞች መካከል ብቻ ተዘዋዋሪ እንዳይሆን ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለዝምድና ባለቤትም፤ አባት ለሌላቸው የቲም ልጆችም፤ ለድሆችና፤ ለመንገደኛ፤ የሚሰጥ ነው:: መልዕክተኛው የሰጣችሁን ሁሉ ማንኛዉም ነገር ያዙት:: የከለከላችሁን ነገር ሁሉም ተከልከሉ:: አላህን ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِلْفُقَرَآءِ ٱلْمُهَٰجِرِينَ ٱلَّذِينَ أُخْرِجُوا۟ مِن دِيَٰرِهِمْ وَأَمْوَٰلِهِمْ يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضْوَٰنًا وَيَنصُرُونَ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلصَّٰدِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy8. ለእነዚያ የአላህን ችሮታና ውዴታውን የሚፈልጉና አላህንና መልዕክተኛውን የሚረዱ ሆነው ከአገሮቻቸውና ከገንዘቦቻቸው ለተወጡ (ለተባረሩ) ስደተኞች ድሆች ይሰጣል:: እነዚያ እነርሱ እውነተኞች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ تَبَوَّءُو ٱلدَّارَ وَٱلْإِيمَٰنَ مِن قَبْلِهِمْ يُحِبُّونَ مَنْ هَاجَرَ إِلَيْهِمْ وَلَا يَجِدُونَ فِى صُدُورِهِمْ حَاجَةً مِّمَّآ أُوتُوا۟ وَيُؤْثِرُونَ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ وَلَوْ كَانَ بِهِمْ خَصَاصَةٌ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِۦ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy9..እነዚያ ከበፊታቸው ሀገሪቱን መዲና መኖሪያ ያደረጓትና እምነት በልባቸው የሰረጸባቸው ወደ እነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ:: ስደተኞችም ከተሰጡት ነገር ላይ በልቦቻቸው ውስጥ እንኳን ምንም ቅሬታን አያሳድሩም:: በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸዉም እንኳ በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ያስቀድማሉ:: ከነፍሶቻቸው ንፉግነት የሚጠበቁ ሰዎች ሁሉ እነዚያ የተሳካለቸውና ምኞታቸውን አግኚዎች ማለት እነርሱ ብቻ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّذِينَ جَآءُو مِنۢ بَعْدِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَا ٱغْفِرْ لَنَا وَلِإِخْوَٰنِنَا ٱلَّذِينَ سَبَقُونَا بِٱلْإِيمَٰنِ وَلَا تَجْعَلْ فِى قُلُوبِنَا غِلًّا لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ رَبَّنَآ إِنَّكَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy10. እነዚያ ከበኋላቸው የመጡት «ጌታችን ሆይ! ለእኛም ለእነዚያም በእምነት ለቀደሙን ወንድሞቻችንም ምህረት አድርግ:: በልቦቻችንም ውስጥ ለእነዚያ ለአመኑት ሰዎች ሁሉ ጥላቻን አታድርግ:: ጌታችን ሆይ! አንተ ሩህሩህ፤ አዛኝ ነህና» ይላሉ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ نَافَقُوا۟ يَقُولُونَ لِإِخْوَٰنِهِمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ لَئِنْ أُخْرِجْتُمْ لَنَخْرُجَنَّ مَعَكُمْ وَلَا نُطِيعُ فِيكُمْ أَحَدًا أَبَدًا وَإِن قُوتِلْتُمْ لَنَنصُرَنَّكُمْ وَٱللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّهُمْ لَكَٰذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያን ወደ ንፍቅና የገቡትን አላወክምን? ከመጽሐፍ ሰዎች መካከል ለእነዚያ ለካዱት ወንድሞቻቸው «ከአገር ብትባርሩ አብረናችሁ እንወጣለን:: በእናንተ ጉዳይ አንድንም ሰው በፍጹም ሁልጊዜም አንታዘዝም:: ጦርነት ቢታወጅባችሁም በእርግጥ እንረዳችኋለን» ይሏቸዋል:: አላህም እነርሱ ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَئِنْ أُخْرِجُوا۟ لَا يَخْرُجُونَ مَعَهُمْ وَلَئِن قُوتِلُوا۟ لَا يَنصُرُونَهُمْ وَلَئِن نَّصَرُوهُمْ لَيُوَلُّنَّ ٱلْأَدْبَٰرَ ثُمَّ لَا يُنصَرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy12. ቢባረሩም አብረዋቸው አይባረሩም:: ቢገደሉም (ቢወጉም) ቢዘመትባቸዉም አይረዱዋቸዉም:: ቢረዷቸዉም ለሽሽት ጀርባዎችን ያዞራሉ:: ከዚያም እርዳታን አያገኙም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَأَنتُمْ أَشَدُّ رَهْبَةً فِى صُدُورِهِم مِّنَ ٱللَّهِ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَفْقَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy13. (እናንተ ያመናችሁ ሆይ!) እናንተ በልቦቻቸው ውስጥ በማስፈራራት ከአላህ ይልቅ የበረታችሁ (የከበዳችሁ) ናችሁ:: ይህም የሆነው እነርሱ የማይገነዘቡ ህዝቦች በመሆናቸው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يُقَٰتِلُونَكُمْ جَمِيعًا إِلَّا فِى قُرًى مُّحَصَّنَةٍ أَوْ مِن وَرَآءِ جُدُرٍۭ بَأْسُهُم بَيْنَهُمْ شَدِيدٌ تَحْسَبُهُمْ جَمِيعًا وَقُلُوبُهُمْ شَتَّىٰ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy14. በተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ወይም ከአጥሮች በስተጀርባ ሆነው እንጂ የተሰበሰቡ ሆነው አይዋጓችሁም:: ኃይላቸው በመካከላቸው ብርቱ ነው:: ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲሆን የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠራጠራቸዋለህ (አንድ ይመስሉሃል):: ይህ እነርሱ አእምሮ የሌላቸው ህዝቦች በመሆናቸው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَمَثَلِ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ قَرِيبًا ذَاقُوا۟ وَبَالَ أَمْرِهِمْ وَلَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy15. ብጤያቸው ልክ እንደነዚያ ከእነርሱ በፊት በቅርብ ጊዜ የተግባራቸውን ቅጣት እንደቀመሱት ወገኖች ብጤ ነው:: ለእነርሱም አሳማሚ ቅጣት አለባቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَمَثَلِ ٱلشَّيْطَٰنِ إِذْ قَالَ لِلْإِنسَٰنِ ٱكْفُرْ فَلَمَّا كَفَرَ قَالَ إِنِّى بَرِىٓءٌ مِّنكَ إِنِّىٓ أَخَافُ ٱللَّهَ رَبَّ ٱلْعَٰلَمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy16. ምሳሌያቸው ልክ እንደዚያ ሰውን «በአላህ ካድ ብሎ ሰውየው በካደ ጊዜ እኔ ካንተ ንጹህ ነኝ እኔ የዓለማትን ጌታ አላህን እፈራለሁ» እንዳለው ሰይጣን ነው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَكَانَ عَٰقِبَتَهُمَآ أَنَّهُمَا فِى ٱلنَّارِ خَٰلِدَيْنِ فِيهَا وَذَٰلِكَ جَزَٰٓؤُا۟ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy17. የሁለቱም መጨረሻቸው እነርሱ በውስጡ ዘወታሪዎች ሲሆኑ በእሳት ውስጥ መሆን ነው:: ይህም ቅጣት የበዳዩች ሁሉ ዋጋ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy18. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን በትክክል ፍሩ:: ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን ትመልከት፤ አላህን በትክክል ፍሩ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَا تَكُونُوا۟ كَٱلَّذِينَ نَسُوا۟ ٱللَّهَ فَأَنسَىٰهُمْ أَنفُسَهُمْ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْفَٰسِقُونَ

Amharic Translation - Africa Academy19. እንደ እነዚያ አላህን እንደረሱትና ነፍሶቻቸውን እንዳስረሳቸው ሰዎች አትሁኑ:: እነዚያ እነርሱ አመጸኞች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَا يَسْتَوِىٓ أَصْحَٰبُ ٱلنَّارِ وَأَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ أَصْحَٰبُ ٱلْجَنَّةِ هُمُ ٱلْفَآئِزُونَ

Amharic Translation - Africa Academy20. የእሳት ጓዶችና የገነት ጓዶች እኩል አይሆኑም:: የገነት ጓዶች ምኞታቸውን አግኝዎች ናቸውና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لَوْ أَنزَلْنَا هَٰذَا ٱلْقُرْءَانَ عَلَىٰ جَبَلٍ لَّرَأَيْتَهُۥ خَٰشِعًا مُّتَصَدِّعًا مِّنْ خَشْيَةِ ٱللَّهِ وَتِلْكَ ٱلْأَمْثَٰلُ نَضْرِبُهَا لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَفَكَّرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy21. (ሙሐመድ ሆይ)፤ ይህንን ቁርኣን በተራራ ላይ ባወረድነው ኖሮ ከአላህ ፍራቻ የተነሳ ተዋራጅና ተሰንጣቂ ሆኖ ባየኸው ነበር:: እነዚህን ምሳሌዎች ለሰዎች ያስተነትኑ ዘንድ እንገልፃቸዋለን::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱللَّهُ ٱلَّذِى لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ هُوَ ٱلرَّحْمَٰنُ ٱلرَّحِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy22. እርሱ ያ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ፤ ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ የሆነ ነው:: እርሱ እጅግ በጣም ሩህሩህ፤ በጣም አዛኝ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱللَّهُ ٱلَّذِى لَآ إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ٱلْمَلِكُ ٱلْقُدُّوسُ ٱلسَّلَٰمُ ٱلْمُؤْمِنُ ٱلْمُهَيْمِنُ ٱلْعَزِيزُ ٱلْجَبَّارُ ٱلْمُتَكَبِّرُ سُبْحَٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy23. እርሱ ያ አላህ ነው:: ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ፤ ንጉሱ፤ ከጎደሎ ሁሉ የጠራ፤ የሰላም ባለቤት፤ ጸጥታን ሰጪ፤ ባሮቹን ጠባቂ፤ አሸናፊ፤ ኃያልና ኩሩ ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱللَّهُ ٱلْخَٰلِقُ ٱلْبَارِئُ ٱلْمُصَوِّرُ لَهُ ٱلْأَسْمَآءُ ٱلْحُسْنَىٰ يُسَبِّحُ لَهُۥ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy24. እርሱ አላህ ፈጣሪዉ፤ ከኢምንት አስገኚዉና ቅርጽን አሳማሪው ነው:: ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት:: በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ እርሱን ያሞግሳል:: እርሱም ሁሉን አሸናፊና ጥበበኛ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70