وَٱلَّذِينَ تَبَوَّءُو ٱلدَّارَ وَٱلْإِيمَٰنَ مِن قَبْلِهِمْ يُحِبُّونَ مَنْ هَاجَرَ إِلَيْهِمْ وَلَا يَجِدُونَ فِى صُدُورِهِمْ حَاجَةً مِّمَّآ أُوتُوا۟ وَيُؤْثِرُونَ عَلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ وَلَوْ كَانَ بِهِمْ خَصَاصَةٌ وَمَن يُوقَ شُحَّ نَفْسِهِۦ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ
Amharic Translation - Africa Academy9..እነዚያ ከበፊታቸው ሀገሪቱን መዲና መኖሪያ ያደረጓትና እምነት በልባቸው የሰረጸባቸው ወደ እነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ:: ስደተኞችም ከተሰጡት ነገር ላይ በልቦቻቸው ውስጥ እንኳን ምንም ቅሬታን አያሳድሩም:: በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸዉም እንኳ በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ያስቀድማሉ:: ከነፍሶቻቸው ንፉግነት የሚጠበቁ ሰዎች ሁሉ እነዚያ የተሳካለቸውና ምኞታቸውን አግኚዎች ማለት እነርሱ ብቻ ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም ከበፊታቸው አገሪቱን መኖሪያ ያደረጉት እምነትንም የለመዱት ወደእነርሱ የተሰደዱትን ሰዎች ይወዳሉ፡፡ (ስደተኞቹ) ከተሰጡትም ነገር በልቦቻቸው ውስጥ ቅሬታን አያገኙም፡፡ በእነርሱ ላይ ችግር ቢኖርባቸውም በነፍሶቻቸው ላይ ሌላውን ይመርጣሉ፡፡ የነፍሱንም ንፍገት የሚጠበቅ ሰው እነዚያ እነሱ ምኞታቸውን አግኚዎች ናቸው፡፡