لَا يُقَٰتِلُونَكُمْ جَمِيعًا إِلَّا فِى قُرًى مُّحَصَّنَةٍ أَوْ مِن وَرَآءِ جُدُرٍۭ بَأْسُهُم بَيْنَهُمْ شَدِيدٌ تَحْسَبُهُمْ جَمِيعًا وَقُلُوبُهُمْ شَتَّىٰ ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَعْقِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy14. በተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ወይም ከአጥሮች በስተጀርባ ሆነው እንጂ የተሰበሰቡ ሆነው አይዋጓችሁም:: ኃይላቸው በመካከላቸው ብርቱ ነው:: ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲሆን የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠራጠራቸዋለህ (አንድ ይመስሉሃል):: ይህ እነርሱ አእምሮ የሌላቸው ህዝቦች በመሆናቸው ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበተመሸጉ ከተሞች ውስጥ ወይም ከአጥሮች ጀርባ ኾነው እንጅ፤ የተሰበሰቡ ኾነው አይዋጉዋችሁም፡፡ ኀይላቸው በመካከላቸው ብርቱ ነው፡፡ ልቦቻቸው የተበታተኑ ሲኾኑ የተሰበሰቡ ናቸው ብለህ ትጠረጥራቸዋለህ፡፡ ይህ እነሱ አእምሮ የሌላቸው ሕዝቦች በመኾናቸው ነው፡፡