أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ نَافَقُوا۟ يَقُولُونَ لِإِخْوَٰنِهِمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ لَئِنْ أُخْرِجْتُمْ لَنَخْرُجَنَّ مَعَكُمْ وَلَا نُطِيعُ فِيكُمْ أَحَدًا أَبَدًا وَإِن قُوتِلْتُمْ لَنَنصُرَنَّكُمْ وَٱللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّهُمْ لَكَٰذِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያን ወደ ንፍቅና የገቡትን አላወክምን? ከመጽሐፍ ሰዎች መካከል ለእነዚያ ለካዱት ወንድሞቻቸው «ከአገር ብትባርሩ አብረናችሁ እንወጣለን:: በእናንተ ጉዳይ አንድንም ሰው በፍጹም ሁልጊዜም አንታዘዝም:: ጦርነት ቢታወጅባችሁም በእርግጥ እንረዳችኋለን» ይሏቸዋል:: አላህም እነርሱ ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደእነዚያ ወደ ነፈቁት አላየህምን? ከመጽሐፉ ሰዎች ውስጥ ለእነዚያ ለካዱት ወንድሞቻቸው (ከአገር) «ብትባረሩ አብረናችሁ እንወጣለን፡፡ በእናንተም (ጉዳይ) አንድንም በፍጹም አንታዘዝም፡፡ ብትገድሉም በእርግጥ እንረዳችኋለን» ይሏቸዋል፡፡ አላህም እነርሱ ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል፡፡