هُوَ ٱلَّذِىٓ أَخْرَجَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْ أَهْلِ ٱلْكِتَٰبِ مِن دِيَٰرِهِمْ لِأَوَّلِ ٱلْحَشْرِ مَا ظَنَنتُمْ أَن يَخْرُجُوا۟ وَظَنُّوٓا۟ أَنَّهُم مَّانِعَتُهُمْ حُصُونُهُم مِّنَ ٱللَّهِ فَأَتَىٰهُمُ ٱللَّهُ مِنْ حَيْثُ لَمْ يَحْتَسِبُوا۟ وَقَذَفَ فِى قُلُوبِهِمُ ٱلرُّعْبَ يُخْرِبُونَ بُيُوتَهُم بِأَيْدِيهِمْ وَأَيْدِى ٱلْمُؤْمِنِينَ فَٱعْتَبِرُوا۟ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَبْصَٰرِ
Amharic Translation - Africa Academy2. እርሱ ያ! ከመጽሐፍ ሰዎች መካከል እነዚያን በአላህ የካዱትን ወገኖች ከቤቶቻቸው የመጀመሪያውን ማስወጣት ያስወጣቸው ነው:: (ሙስሊሞች ሆይ!) መውጣታቸውንም አላሰባችሁትም ነበር:: እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ ኃይል የሚከላከሉላቸው መሆናቸውን አሰቡ:: አላህ ግን ካላሰቡት በኩል መጣባቸው:: እናም በልቦቻቸው ውስጥ መርበድበድን (ፍርሃትን) ጣለባቸው:: ቤቶቻቸውን በገዛ እጆቻቸውና በትክክለኛ አማኞች እጅ ያፈርሳሉ (አፈረሱ):: እናንተ የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ! አስተውሉ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱ ያ ከመጽሐፉ ሰዎች እነዚያን የካዱትን ከቤቶቻቸው ለመጀመሪያው ማውጣት ያወጣቸው ነው፡፡ መውጣታቸውን አላሰባችሁም፡፡ እነርሱም ምሽጎቻቸው ከአላህ (ኀይል) የሚከላከሉላቸው መኾናቸውን አሰቡ፡፡ አላህም ካላሰቡት ስፍራ መጣባቸው፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ መርበድበድን ጣለባቸው፡፡ ቤቶቻቸውን በእጆቻቸውና በምእምናኖቹ እጆች ያፈርሳሉ፡፡ አስተውሉም የአእምሮ ባለቤቶች ሆይ!