caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Hashr፣ አንቀጽ 7

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 101 · 59:7

مَّآ أَفَآءَ ٱللَّهُ عَلَىٰ رَسُولِهِۦ مِنْ أَهْلِ ٱلْقُرَىٰ فَلِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَٰمَىٰ وَٱلْمَسَٰكِينِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ كَىْ لَا يَكُونَ دُولَةًۢ بَيْنَ ٱلْأَغْنِيَآءِ مِنكُمْ وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Amharic Translation - Africa Academy7. አላህ ከከተሞች ሰዎች ሀብት መካከል በመልዕክተኛው ላይ የመለሰው ሀብት ከናንተ ውስጥ በሀብታሞች መካከል ብቻ ተዘዋዋሪ እንዳይሆን ለአላህና ለመልዕክተኛው፤ ለዝምድና ባለቤትም፤ አባት ለሌላቸው የቲም ልጆችም፤ ለድሆችና፤ ለመንገደኛ፤ የሚሰጥ ነው:: መልዕክተኛው የሰጣችሁን ሁሉ ማንኛዉም ነገር ያዙት:: የከለከላችሁን ነገር ሁሉም ተከልከሉ:: አላህን ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ከከተሞቹ ሰዎች (ሀብት) በመልክተኛው ላይ የመለሰው (ሀብት) ከእናንተ ውስጥ በሀብታሞቹ መካከል ተዘዋዋሪ እንዳይኾን፡፡ ለአላህና ለመልክተኛው፣ ለዝምድና ባለቤትም፣ አባት ለሌላቸው ልጆችም፣ ለድኾችም፣ ለመንገደኛም (የሚስሰጥ) ነው፡፡ መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70