ٱلَّذِينَ يُجَٰدِلُونَ فِىٓ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَٰنٍ أَتَىٰهُمْ كَبُرَ مَقْتًا عِندَ ٱللَّهِ وَعِندَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كَذَٰلِكَ يَطْبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ قَلْبِ مُتَكَبِّرٍ جَبَّارٍ
Amharic Translation - Africa Academy35. እነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ ታዓምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም ያመኑት ዘንድ መጠላቱ በጣም ተለቀ:: እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ ልብ ሁሉ ላይ ያትማል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ፤ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ ተዓምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም አመኑት ዘንድ መጠላቱ በጣም ተለቀ፡፡ እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ (ሰው) ልብ ሁሉ ላይ ያትማል፡፡