أَوَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ كَانُوا۟ مِن قَبْلِهِمْ كَانُوا۟ هُمْ أَشَدَّ مِنْهُمْ قُوَّةً وَءَاثَارًا فِى ٱلْأَرْضِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمْ وَمَا كَانَ لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن وَاقٍ
Amharic Translation - Africa Academy21. የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ፍፃሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይሄዱምን? በሀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶች ከእነርሱም ይበልጥ የበረቱ ነበሩ:: አላህም በኃጢአቶቻቸው ያዛቸው። ለእነርሱም ከአላህ ቅጣት ምንም ጠባቂ አልነበራቸዉም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይኼዱምን? በኀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶች፤ ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ነበሩ፡፡ አላህም በኀጢአቶቻቸው ያዛቸው፡፡ ለእነርሱም ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ አልነበራቸውም፡፡