caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Ghaafir፣ አንቀጽ 7

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 60 · 40:7

ٱلَّذِينَ يَحْمِلُونَ ٱلْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُۥ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِۦ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَىْءٍ رَّحْمَةً وَعِلْمًا فَٱغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا۟ وَٱتَّبَعُوا۟ سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ ٱلْجَحِيمِ

Amharic Translation - Africa Academy7. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፤ በእርሱም ያምናሉ። ለነዚያ ላመኑትም (እንዲህ እያሉ) ምህረትን ይለምኑላቸዋል: «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በእውቀት ከበሃል፤ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምህረት አድርግላቸው፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፤
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በዕውቀት ከበሃል፡፡ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፡፡» እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70