وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ وَإِن تَدْعُ مُثْقَلَةٌ إِلَىٰ حِمْلِهَا لَا يُحْمَلْ مِنْهُ شَىْءٌ وَلَوْ كَانَ ذَا قُرْبَىٰٓ إِنَّمَا تُنذِرُ ٱلَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُم بِٱلْغَيْبِ وَأَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَمَن تَزَكَّىٰ فَإِنَّمَا يَتَزَكَّىٰ لِنَفْسِهِۦ وَإِلَى ٱللَّهِ ٱلْمَصِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy18. ኃጢአትን ተሸካሚም ነፍስ የሌላውን ሸክም አትሸከምም:: የራሷ ወንጀል የከበዳትም ነፍስ እርዳታ እንዲደረግላት ብትጠራ ተጠሪው የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳን ከእርሷ አንድን ነገር የሚሸከምላት አታገኝም:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን፤ በሩቅ የሚፈሩትን ሶላትንም አስተካክለው የሚሰገዱትን ብቻ ነው:: ከወንጀልም የተጥራራ ሁሉ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው:: መመለሻዉም ወደ አላህ ብቻ ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqኀጢአትን ተሸካሚም (ነፍስ) የሌላዋን ሸክም አትሸከምም፡፡ የተከበደችም (ነፍስ) ወደ ሸክሟ ብትጣራ (ተጠሪው) የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢኾንም እንኳ ከእርሷ አንዳችን የሚሸከምላት አታገኝም፡፡ የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን በሩቅ የሚፈሩትን፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱትን ብቻ ነው፡፡ የተጥራራም ሰው የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡