ٱسْلُكْ يَدَكَ فِى جَيْبِكَ تَخْرُجْ بَيْضَآءَ مِنْ غَيْرِ سُوٓءٍ وَٱضْمُمْ إِلَيْكَ جَنَاحَكَ مِنَ ٱلرَّهْبِ فَذَٰنِكَ بُرْهَٰنَانِ مِن رَّبِّكَ إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَمَلَإِي۟هِۦٓ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمًا فَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy32. "እጅህን በአንገትጌህ ውስጥ አስግባ:: ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና፤ ክንፍህንም ከፍርሃት ለመዳን ወደ አንተ አጣብቅ:: እነዚህም ከጌታህ የሆኑ ወደ ፈርዖንና ወደ መኳንቶች የሚደርሱ ሁለት አስረጅዎች ናቸው:: እነርሱ አመጠኞች ህዝቦች ነበሩና።“
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«እጅህን በአንገትጌህ ውስጥ አግባ፡፡ ያለ ነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና፡፡ ክንፍህንም ከፍርሃት (ለመዳን) ወዳንተ አጣብቅ፡፡ እነዚህም ከጌታህ የሆኑ ወደ ፈርዖንና ወደ መኳንንቶቹ የሚደርሱ ሁለት አስረጅዎች ናቸው፡፡ እነርሱ አመጸኞች ሕዝቦች ነበሩና፡፡»