caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Qasas፣ አንቀጽ 15

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 49 · 28:15

وَدَخَلَ ٱلْمَدِينَةَ عَلَىٰ حِينِ غَفْلَةٍ مِّنْ أَهْلِهَا فَوَجَدَ فِيهَا رَجُلَيْنِ يَقْتَتِلَانِ هَٰذَا مِن شِيعَتِهِۦ وَهَٰذَا مِنْ عَدُوِّهِۦ فَٱسْتَغَٰثَهُ ٱلَّذِى مِن شِيعَتِهِۦ عَلَى ٱلَّذِى مِنْ عَدُوِّهِۦ فَوَكَزَهُۥ مُوسَىٰ فَقَضَىٰ عَلَيْهِ قَالَ هَٰذَا مِنْ عَمَلِ ٱلشَّيْطَٰنِ إِنَّهُۥ عَدُوٌّ مُّضِلٌّ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy15. ሙሳ ከተማይቱንም ሰዎቿ በዝንጋቴ ላይ ሆነው ሳሉ ገባ:: በእርሷም ውስጥ የሚጋደሉን ሁለት ሰዎች አገኘ:: ይህ (አንዱ) ከወገኑ ነው፤ ይህ (ሌላው) ደግሞ ከጠላቱ ነው፤ ያ ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጣላት በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው:: ሙሳም በጡጫ መታው:: ገደለዉም:: “ይህ ከሰይጣን ስራ ነው:: እርሱ ግልጽ አሣሣች ጠላት ነውና” አለ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከተማይቱንም ሰዎቿ በዝንጋቴ ጊዜ ላይ ሆነው ሳሉ ገባ፡፡ በእርሷም ውስጥ የሚጋደሉን ሁለት ሰዎችን አገኘ፡፡ ይህ ከወገኑ ነው፤ ይህም ከጠላቱ ነው፡፡ ያም ከወገኑ የሆነው ሰው በዚያ ከጠላቱ በሆነው ሰው ላይ እርዳታን ጠየቀው፡፡ ሙሳም በጡጫ መታው፡፡ ገደለውም፡፡ ይህ ከሰይጣን ሥራ ነው፡፡ እርሱ ግልጽ አሳሳች ጠላት ነውና አለ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70