وَلَا تَنفَعُ ٱلشَّفَٰعَةُ عِندَهُۥٓ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُۥ حَتَّىٰٓ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمْ قَالُوا۟ مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ قَالُوا۟ ٱلْحَقَّ وَهُوَ ٱلْعَلِىُّ ٱلْكَبِيرُ
Amharic Translation - Africa Academy23. ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም:: ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጠ ጊዜ ተማላጆቹ «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ:: አማላጆቹም: «እውነትን አለ። እርሱም ከፍተኛውና ታላቁ ጌታ ነው።» ይላሉ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፡፡ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ (ተማላጆቹ) «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ፡፡ (አማላጆቹ) «እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው» ይላሉ፡፡