caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Saba፣ አንቀጽ 3

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 58 · 34:3

وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَا تَأْتِينَا ٱلسَّاعَةُ قُلْ بَلَىٰ وَرَبِّى لَتَأْتِيَنَّكُمْ عَٰلِمِ ٱلْغَيْبِ لَا يَعْزُبُ عَنْهُ مِثْقَالُ ذَرَّةٍ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَلَا فِى ٱلْأَرْضِ وَلَآ أَصْغَرُ مِن ذَٰلِكَ وَلَآ أَكْبَرُ إِلَّا فِى كِتَٰبٍ مُّبِينٍ

Amharic Translation - Africa Academy3. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) እነዚያ በአላህ የካዱትም ሰዎች «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡ «ጉዳዩ እንዳሰባችሁት አይደለም። ሩቁን ሁሉ አዋቂ በሆነው ጌታዬ እምላለሁ:: በእርግጥ ትመጣባችኋለች:: የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእሱ አይሰወርም አይርቅም:: ከዚህ ያነሰም ሆነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጂ::» በላቸው
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያ የካዱትም «ሰዓቲቱ አትመጣብንም» አሉ፡፡ በላቸው «አይደለም፤ ሩቁን ሁሉ ዐዋቂ በኾነው ጌታዬ እምላለሁ፡፡ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፡፡ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳ በሰማያትና በምድር ውስጥ ከእርሱ አይርቅም፡፡ ከዚህ ያነሰም ኾነ የበለጠ የለም በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢኾን እንጅ፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70