caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Saba፣ አንቀጽ 12

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 58 · 34:12

وَلِسُلَيْمَٰنَ ٱلرِّيحَ غُدُوُّهَا شَهْرٌ وَرَوَاحُهَا شَهْرٌ وَأَسَلْنَا لَهُۥ عَيْنَ ٱلْقِطْرِ وَمِنَ ٱلْجِنِّ مَن يَعْمَلُ بَيْنَ يَدَيْهِ بِإِذْنِ رَبِّهِۦ وَمَن يَزِغْ مِنْهُمْ عَنْ أَمْرِنَا نُذِقْهُ مِنْ عَذَابِ ٱلسَّعِيرِ

Amharic Translation - Africa Academy12. ለሱለይማንም ንፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ፤ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲሆን ገራንለት:: የነሀስንም ምንጭ ለእርሱ አፈሰስንለት:: ከአጋንንቶችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሰሩትን (አደረግንለት):: ከእነርሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዳጅ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለሱለይማንም ነፋስን የቀትር በፊት ጉዞዋ የወር መንገድ የቀትር በኋላ ጉዞዋም የወር መንገድ ሲኾን ገራንለት፡፡ የነሐስንም ምንጭ ለእርሱ አፈሰስንለት፡፡ ከጋኔኖችም በጌታው ፈቃድ በፊቱ የሚሠሩን (አደረግንለት)፡፡ ከነርሱም ውስጥ ከትእዛዛችን ዝንፍ የሚል ከነዲድ እሳት ቅጣት እናቀምሰዋለን፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70