وَإِذْ قَالَ لُقْمَٰنُ لِٱبْنِهِۦ وَهُوَ يَعِظُهُۥ يَٰبُنَىَّ لَا تُشْرِكْ بِٱللَّهِ إِنَّ ٱلشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገስጸው ሲሆን «ልጄ ሆይ! በአላህ አታጋራ። ማጋራት ታላቅ በደል ነውና።» ያለውን አስታውስ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን «ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና» ያለውን (አስታውስ)፡፡