يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُوا۟ رَبَّكُمْ وَٱخْشَوْا۟ يَوْمًا لَّا يَجْزِى وَالِدٌ عَن وَلَدِهِۦ وَلَا مَوْلُودٌ هُوَ جَازٍ عَن وَالِدِهِۦ شَيْـًٔا إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ فَلَا تَغُرَّنَّكُمُ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا وَلَا يَغُرَّنَّكُم بِٱللَّهِ ٱلْغَرُورُ
Amharic Translation - Africa Academy33. እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ:: ወላጅ ከልጁ በምንም የማይጠቅምበት ልጅም ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ:: የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና:: ቅርቢቱም ህይወት አትሸንግላችሁ:: በአላህ (መታገስም) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ወላጅም ከልጁ (በምንም) የማይጠቅምበትን፤ ተወላጅም እርሱ ወላጅን በምንም ጠቃሚ የማይሆንበትን ቀን ፍሩ፡፡ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት አትሸንግላችሁ፡፡ በአላህም (መታገስ) አታላዩ (ሰይጣን) አያታልላችሁ፡፡