هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ يَعْلَمُ مَا يَلِجُ فِى ٱلْأَرْضِ وَمَا يَخْرُجُ مِنْهَا وَمَا يَنزِلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا يَعْرُجُ فِيهَا وَهُوَ مَعَكُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy4. እርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ብቻ የፈጠረ ነው:: ከዚያ በዐርሹ ላይ ከፍ አለ። ወደ ምድር የሚገባውንና ከእርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: ከሰማይ የሚወረደውንና ወደ እርሷ የሚወጣውን ያውቃል:: እርሱ የትም ብትሆኑ (በእውቀቱ) ከናንተው ጋር ነው:: አላህ የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ (ለሱ ክብር በሚስማማ መልኩ)የተደላደለ ነው፡፡ በምድር ውስጥ የሚገባውን፣ ከእርሷም የሚወጣውን፣ ከሰማይም የሚወርደውን በእርሷም ውስጥ የሚያርገውን ያውቃል፡፡ እርሱም የትም ብትኾኑ ከእናንተ ጋር ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡