يُنَادُونَهُمْ أَلَمْ نَكُن مَّعَكُمْ قَالُوا۟ بَلَىٰ وَلَٰكِنَّكُمْ فَتَنتُمْ أَنفُسَكُمْ وَتَرَبَّصْتُمْ وَٱرْتَبْتُمْ وَغَرَّتْكُمُ ٱلْأَمَانِىُّ حَتَّىٰ جَآءَ أَمْرُ ٱللَّهِ وَغَرَّكُم بِٱللَّهِ ٱلْغَرُورُ
Amharic Translation - Africa Academy14. "ከናንተ ጋር አልነበርንምን?" በማለት ይጠሯቸዋል:: "እውነት ነው እኛ ጋር ነበራችሁ:: ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ:: በነብዩ አደጋዎችን ተጠባበቃችሁ ትጠራጠራላችሁም:: የአላህ ትዕዛዝ እስከ መጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ። አታላዩም ሰይጣን በአላህ መታገስ ሸነገላችሁ ይሏቸዋል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ከእናንተ ጋር አልነበርንምን?» በማለት ይጠሩዋቸዋል፡፡ «እውነት ነው፡፡ ግን እናንተ ነፍሶቻችሁን አጠፋችሁ፡፡ (በነቢዩ አደጋዎችን) ተጠባበቃችሁም፡፡ ተጠራጠራችሁም፡፡ የአላህም ትዕዛዝ እስከ መጣ ድረስ ከንቱ ምኞቶች አታለሏችሁ፡፡ አታላዩም (ሰይጣን) በአላህ (መታገስ) ሸነገላችሁ፤» ይሏቸዋል፡፡