ثُمَّ قَفَّيْنَا عَلَىٰٓ ءَاثَٰرِهِم بِرُسُلِنَا وَقَفَّيْنَا بِعِيسَى ٱبْنِ مَرْيَمَ وَءَاتَيْنَٰهُ ٱلْإِنجِيلَ وَجَعَلْنَا فِى قُلُوبِ ٱلَّذِينَ ٱتَّبَعُوهُ رَأْفَةً وَرَحْمَةً وَرَهْبَانِيَّةً ٱبْتَدَعُوهَا مَا كَتَبْنَٰهَا عَلَيْهِمْ إِلَّا ٱبْتِغَآءَ رِضْوَٰنِ ٱللَّهِ فَمَا رَعَوْهَا حَقَّ رِعَايَتِهَا فَـَٔاتَيْنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنْهُمْ أَجْرَهُمْ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ فَٰسِقُونَ
Amharic Translation - Africa Academy27. ከዚያም በእነርሱ ፈለጋቸው ላይ መልዕክተኞችን አከታተልን:: የመርየም ልጅን ዒሳንም አስከተልን:: ኢንጂልንም ሰጠነው:: በእነዚያም በተከተሉት ሰዎች ልቦች ውስጥ መለዘብንና እዝነትን አደረግን፤ አዲስ የፈጠሯትንም ምንኩስና በእነርሱ ላይ አልደነገግንም:: ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ ከራሳቸው ፈጠሯት:: ተገቢ አጠባበቅንም አልጠበቋትም:: ከእነርሱም መካከል በአላህ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው:: ከእነርሱ ብዙዎቹ ግን አመጸኞች ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከዚያም በዱካዎቻቸው ላይ መልክተኞቻችንን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም አስከተልን፡፡ ኢንጂልንም ሰጠነው፡፡ በእነዚያም በተከተሉት (ሰዎች) ልቦች ውሰጥ መለዘብንና እዝነትን፣ አዲስ የፈጠሩዋትንም ምንኩስና አደረግን፡፡ በእነርሱ ላይ (ምንኩስናን) አልጻፍናትም፡፡ ግን የአላህን ውዴታ ለመፈለግ ሲሉ (ፈጠሩዋት)፡፡ ተገቢ አጠባበቋንም፤ አልጠበቋትም፡፡ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጠናቸው፡፡ ከእነርሱም ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፡፡