caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Hadid፣ አንቀጽ 20

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 94 · 57:20

ٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا لَعِبٌ وَلَهْوٌ وَزِينَةٌ وَتَفَاخُرٌۢ بَيْنَكُمْ وَتَكَاثُرٌ فِى ٱلْأَمْوَٰلِ وَٱلْأَوْلَٰدِ كَمَثَلِ غَيْثٍ أَعْجَبَ ٱلْكُفَّارَ نَبَاتُهُۥ ثُمَّ يَهِيجُ فَتَرَىٰهُ مُصْفَرًّا ثُمَّ يَكُونُ حُطَٰمًا وَفِى ٱلْـَٔاخِرَةِ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَغْفِرَةٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضْوَٰنٌ وَمَا ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَآ إِلَّا مَتَٰعُ ٱلْغُرُورِ

Amharic Translation - Africa Academy20. (ሰዎች ሆይ!) ቅርቢቱን ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፤ ማጌጫም፤ በመካከችሁም መፎካከሪያ፤ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መሆኗን እወቁ:: እርሷ በቃዩ ገበሬዎችን ቡቃያው እንደሚያስደስት ዝናብና ከዚያ በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደሚታየው ከዚም የተሰባበረ እንደሚሆን ብጤ ነው:: በመጨረሻይቱም ዓለም ለአጥፊዎች ብርቱ ቅጣት፤ ለትክክለኛ አማኞች ከአላህ ምህረትና ውዴታ አለ:: የቅርቢቱ ሕይወት እኮ የመታለያ ጥቅም እንጂ ሌላ አይደለችም::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqቅርቢቱ ሕይወት ጨዋታና ዛዛታ፣ ማጌጫም፣ በመካከላችሁም መፎካከሪያ፣ በገንዘቦችና በልጆችም ብዛት መበላለጫ ብቻ መኾንዋን ዕወቁ፡፡ (እርሷ) በቃዩ ገበሬዎችን እንደሚያስደስት ዝናም፣ ከዚያም በቃዩ እንደሚደርቅና ገርጥቶ እንደምታየው፣ ከዚያም የተሰባበረ እንደሚኾን ብጤ ናት፣ በመጨረሻይቱም ዓለም ብርቱ ቅጣት ከአላህም ምሕረትና ውዴታ አልለ፡፡ የቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ ጥቅም እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70