يَوْمَ يَقُولُ ٱلْمُنَٰفِقُونَ وَٱلْمُنَٰفِقَٰتُ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱنظُرُونَا نَقْتَبِسْ مِن نُّورِكُمْ قِيلَ ٱرْجِعُوا۟ وَرَآءَكُمْ فَٱلْتَمِسُوا۟ نُورًا فَضُرِبَ بَيْنَهُم بِسُورٍ لَّهُۥ بَابٌۢ بَاطِنُهُۥ فِيهِ ٱلرَّحْمَةُ وَظَٰهِرُهُۥ مِن قِبَلِهِ ٱلْعَذَابُ
Amharic Translation - Africa Academy13. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የወንድ አስመሳዮችና የሴት አስመሳዮች ለእነዚያ በአላህ ላመኑት "ጠብቁን ከብርሀናችሁ እናበራለንና" የሚሉበትን ቀን አስታውስ:: "ወደ ኋላችሁ ተመለሱ:: ብርሀንንም እዚያው ፈልጉ" ይባላሉ:: በመካከላቸዉም ለእርሱ ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል:: ግቢው በውስጡ ገነት ያለበት ከውጪዉም በኩሉ ደግሞ የእሳት (ስቃይ) ያለበት የሆነ (ደጃፍ ባለው አጥር ይከለላል)።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመናፍቃንና መናፍቃት ለእነዚያ ለአመኑት «ተመልከቱን፤ ከብርሃናችሁ እናበራለንና» የሚሉበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ «ወደ ኋላችሁ ተመለሱ፡፡ ብርሃንንም ፈልጉ» ይባላሉ፡፡ ግቢው በውስጡ ችሮታ (ገነት) ያለበት ውጭውም ከበኩሉ ስቃይ (እሳት) ያለበት የኾነ (ደጃፍ ባለው አጥር)፡፡