يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱجْتَنِبُوا۟ كَثِيرًا مِّنَ ٱلظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ ٱلظَّنِّ إِثْمٌ وَلَا تَجَسَّسُوا۟ وَلَا يَغْتَب بَّعْضُكُم بَعْضًا أَيُحِبُّ أَحَدُكُمْ أَن يَأْكُلَ لَحْمَ أَخِيهِ مَيْتًا فَكَرِهْتُمُوهُ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ إِنَّ ٱللَّهَ تَوَّابٌ رَّحِيمٌ
Amharic Translation - Africa Academy12. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙን ራቁ:: ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና:: ነውርንም አትከታተሉ። ከፊላችሁም ከፊሉን አይማው። አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ሆኖ ሊበላ ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁት (ሀሜቱንም ጥሉት):: አላህንም ፍሩ:: አላህ ጸጸትን ተቀባይና አዛኝ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ፤ ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡ ነውርንም አትከታተሉ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ፡፡ አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡