يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَرْفَعُوٓا۟ أَصْوَٰتَكُمْ فَوْقَ صَوْتِ ٱلنَّبِىِّ وَلَا تَجْهَرُوا۟ لَهُۥ بِٱلْقَوْلِ كَجَهْرِ بَعْضِكُمْ لِبَعْضٍ أَن تَحْبَطَ أَعْمَٰلُكُمْ وَأَنتُمْ لَا تَشْعُرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ድምፆቻችሁን ከነብዩ ድምጽ በላይ ከፍ አታድርጉ:: ከፊላችሁ ለከፊሉ እንደሚጮህም ሁሉ በንግግር ለርሱ ስትናገሩ አትጩሁ:: እናንተ የማታውቁ ስትሆኑ ስራዎቻችሁ እንዳይበላሹ (ከዚህ ተከልከሉ)::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ድምጾቻችሁን ከነቢዩ ድምጽ በላይ ከፍ አታድርጉ፡፡ ከፊላችሁም ለከፊሉ እንደሚጮህ በንግግር ለርሱ አትጩሁ፡፡ እናንተ የማታውቁ ስትኾኑ ሥራዎቻችሁ እንዳይበላሹ (ተከልከሉ)፡፡