وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ فِيكُمْ رَسُولَ ٱللَّهِ لَوْ يُطِيعُكُمْ فِى كَثِيرٍ مِّنَ ٱلْأَمْرِ لَعَنِتُّمْ وَلَٰكِنَّ ٱللَّهَ حَبَّبَ إِلَيْكُمُ ٱلْإِيمَٰنَ وَزَيَّنَهُۥ فِى قُلُوبِكُمْ وَكَرَّهَ إِلَيْكُمُ ٱلْكُفْرَ وَٱلْفُسُوقَ وَٱلْعِصْيَانَ أُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلرَّٰشِدُونَ
Amharic Translation - Africa Academy7. በውስጣችሁም የአላህ መልዕክተኛ መኖሩን እወቁ:: ከነገሩ በብዙው ነገሮች ቢከተላችሁ ኖሮ በእርግጥ በተቸገራችሁ ነበር:: ግን አላህ እምነትን ወደ እናንተ አስወደደ :: በልቦቻችሁም ውስጥ አስዋበው። ክህደትን፣ አመፅንና እምቢተኝነትንም ለናንተ የተጠላ አደረገ። እነዚያ እምነትን የወደዱና ክሕደትን የጠሉ ሰዎች እነርሱ ትክክለኛ ቅኖቹ ናቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበውስጣችሁም የአላህ መልክተኛ መኖሩን ዕወቁ፡፡ ከነገሩ በብዙው ቢከተላችሁ ኖሮ በእርግጥ በተቸገራችሁ ነበር፡፡ ግን አላህ አምነትን ወደናንተ አስወደደ፡፡ በልቦቻችሁም ውሰጥ አጌጠው፡፡ ክህደትንና አመጽንም እንቢተኛነትንም ወደናንተ የተጠላ አደረገ፡፡ እነዚያ (እምነትን የወደዱና ክሕደተን የጠሉ) እነርሱ ቅኖቹ ናቸው፡፡