يَمُنُّونَ عَلَيْكَ أَنْ أَسْلَمُوا۟ قُل لَّا تَمُنُّوا۟ عَلَىَّ إِسْلَٰمَكُم بَلِ ٱللَّهُ يَمُنُّ عَلَيْكُمْ أَنْ هَدَىٰكُمْ لِلْإِيمَٰنِ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy17. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በመስለማቸው ባንተ ላይ ይመፃደቃሉ። «በእስልምናችሁ በእኔ ላይ አትመጻደቁ:: ይልቁንም አላህ ወደ ትክክለኛው እምነት ስለመራችሁ ፀጋውን ውሎላችኋል:: እውነተኞች ብትሆኑ (መመፃደቅ የሚገባው ለአላህ) ብቻ ነው» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበመስለማቸው በአንተ ላይ ይመጻደቃሉ «በስልምናችሁ በኔ ላይ አትመጻደቁ፤ ይልቁንም አላህ ወደ እምነት ስለ መራችሁ ይመጸደቅባችኋል፤ እውነተኞች ብትኾኑ» (መመጻደቅ ለአላህ ነው) በላቸው፡፡