لَّقَدْ صَدَقَ ٱللَّهُ رَسُولَهُ ٱلرُّءْيَا بِٱلْحَقِّ لَتَدْخُلُنَّ ٱلْمَسْجِدَ ٱلْحَرَامَ إِن شَآءَ ٱللَّهُ ءَامِنِينَ مُحَلِّقِينَ رُءُوسَكُمْ وَمُقَصِّرِينَ لَا تَخَافُونَ فَعَلِمَ مَا لَمْ تَعْلَمُوا۟ فَجَعَلَ مِن دُونِ ذَٰلِكَ فَتْحًا قَرِيبًا
Amharic Translation - Africa Academy27. ህልሙ እውነተኛ ሲሆን አላህ የፈለገ አንደሆነ ጸጥተኞች ሆናችሁ ራሳችሁን ላጭታችሁ አሳጥራችሁ የማትፈሩ ስትሆኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ ያለውን ህልም አሏህ ለመልዕክተኛው(ለሙሀመድ) እውነት አደረገለት:: አላህ (ከእርቁ) ከመመለሳችሁ ሂደት ያላወቃችሁትንም ነገር አወቀ:: እናም ከዚህ በፊት ቅርብን የመክፈት እርቅ አደረገ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ለመልክተኛው ሕልሙን እውነተኛ ሲኾን አላህ የሻ እንደ ኾነ ጸጥተኞች ኾናችሁ ራሶቻችሁን ላጭታችሁ፣ አሳጥራችሁም የማትፈሩ ስትኾኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ፤ ያለውን በእርግጥ እውነት አደረገለት፡፡ (ከእርቁ) ያላወቃችሁትንም ነገር ዐወቀ፡፡ ከዚህም በፊት ቅርብን መክፈት አደረገ፡፡