سَيَقُولُ ٱلْمُخَلَّفُونَ إِذَا ٱنطَلَقْتُمْ إِلَىٰ مَغَانِمَ لِتَأْخُذُوهَا ذَرُونَا نَتَّبِعْكُمْ يُرِيدُونَ أَن يُبَدِّلُوا۟ كَلَٰمَ ٱللَّهِ قُل لَّن تَتَّبِعُونَا كَذَٰلِكُمْ قَالَ ٱللَّهُ مِن قَبْلُ فَسَيَقُولُونَ بَلْ تَحْسُدُونَنَا بَلْ كَانُوا۟ لَا يَفْقَهُونَ إِلَّا قَلِيلًا
Amharic Translation - Africa Academy15. ከጠላት የተማረኩትን ገንዘቦች ልትይዙ በሄዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች «ተውን እንከተላችሁ» ይሏችኋል:: በዚህም የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ:: «ፈጽሞ አትከተሉንም:: ልክ እንደዚሃችሁ ቃል የመሰለ ከዚህ በፊት አላህም ብሏል» በሏቸው:: «ይልቁንም ትመቀኙናላችሁ» ይላሉም:: በእውነት እነርሱም ጥቂትን እንጂ የማያውቁ ነበሩ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqወደ ምርኮዎች ልትይዟት በኼዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች «ተዉን እንከተላችሁ» ይሏችኋል፡፡ (በዚህም) የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ፡፡ «ፈጽሞ አትከተሉንም፡፡ ይህን (ቃል) ከዚህ በፊት አላህ ብሏል» በላቸው፡፡ ይልቁንም «ትመቀኙናላችሁ» ይላሉም፡፡ በእውነት እነርሱ ጥቂትን እንጅ የማያውቁ ነበሩ፡፡