هُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ وَصَدُّوكُمْ عَنِ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَٱلْهَدْىَ مَعْكُوفًا أَن يَبْلُغَ مَحِلَّهُۥ وَلَوْلَا رِجَالٌ مُّؤْمِنُونَ وَنِسَآءٌ مُّؤْمِنَٰتٌ لَّمْ تَعْلَمُوهُمْ أَن تَطَـُٔوهُمْ فَتُصِيبَكُم مِّنْهُم مَّعَرَّةٌۢ بِغَيْرِ عِلْمٍ لِّيُدْخِلَ ٱللَّهُ فِى رَحْمَتِهِۦ مَن يَشَآءُ لَوْ تَزَيَّلُوا۟ لَعَذَّبْنَا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنْهُمْ عَذَابًا أَلِيمًا
Amharic Translation - Africa Academy25. እነርሱ ማለት እነዚያ በአላህ የካዱ፤ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ መስዋዕትንም የታሰረ ሲሆን ወደ ስፍራው እንዳይደርስ የከለከሉ ናቸው:: የማታውቋቸው ወንድ አማኞችና ሴት ምዕመናት ከከሓዲያኑ ጋር ባልነበሩ ኖሮና እናንተም ያለ እውቀት እነርሱን ረግጣችሁ ከእነርሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባይሆን ኖሮ እጆቻችሁን ባላገድን ነበር:: አላህም የሚፈልገውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያስገባ ዘንድ (እጆቻችሁን አገደ):: በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእርሱ ውስጥ በአላህ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነርሱ እነዚያ የካዱ፣ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ፣ መስዋእቱንም የታሰረ ሲኾን በስፍራው እንዳይደርስ (የከለከሉ) ናቸው፡፡ የማታውቋቸው የኾኑ ምእመናን ወንዶችና ምእምናት ሴቶች (ከከሓዲዎቹ ጋር) ባልነበሩ ያለ ዕውቀት እነርሱን መርገጣችሁና ከእነርሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባልኾነ ኖሮ (እጆቻችሁን ባላገድን ነበር) አላህ የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያገባ ዘንድ (እጆቻችሁን አገደ)፡፡ በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእነርሱ ውስጥ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር፡፡