مُّحَمَّدٌ رَّسُولُ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ مَعَهُۥٓ أَشِدَّآءُ عَلَى ٱلْكُفَّارِ رُحَمَآءُ بَيْنَهُمْ تَرَىٰهُمْ رُكَّعًا سُجَّدًا يَبْتَغُونَ فَضْلًا مِّنَ ٱللَّهِ وَرِضْوَٰنًا سِيمَاهُمْ فِى وُجُوهِهِم مِّنْ أَثَرِ ٱلسُّجُودِ ذَٰلِكَ مَثَلُهُمْ فِى ٱلتَّوْرَىٰةِ وَمَثَلُهُمْ فِى ٱلْإِنجِيلِ كَزَرْعٍ أَخْرَجَ شَطْـَٔهُۥ فَـَٔازَرَهُۥ فَٱسْتَغْلَظَ فَٱسْتَوَىٰ عَلَىٰ سُوقِهِۦ يُعْجِبُ ٱلزُّرَّاعَ لِيَغِيظَ بِهِمُ ٱلْكُفَّارَ وَعَدَ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِنْهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًۢا
Amharic Translation - Africa Academy29. የአላህ መልዕክተኛ (ነብዩ) ሙሐመድ እና እነዚያም የእርሱ ጓደኞች በከሓዲያን ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው ተዛዛኞች ናቸው:: አጎንባሾች፤ ሰጋጆች፤ ሆነው ታያቸዋልህ:: ችሮታንና ውዴታን ሁልጊዜም ከአላህ ይፈልጋሉ:: ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትሆን በፊታቸው ላይ ናት:: ይህ በተውራት (የተነገረላቸው) ጸባያቸው ነው:: በኢንጅል ውስጥ የተጠቀሰው ምሳሌያቸው ደግሞ ቀንዘሉን እንደ አወጣ አዝመራና (ቀንዘሉን) እንዳበረታው እንደ ወፍራምና ገበሬዎቹን የሚያስደነቅ ሆኖ አገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደቆመ (አዝመራ) ነው:: ያበረታቸውና ከሓዲያን በእርሱ ሊያሰቆጭ ነው:: አላህ እነዚያን በእሱ ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን ተግባራት የሰሩትን ሁሉ ምህረትንና ታላቅ ምንዳን ቃል ገበቶላቸዋል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqየአላህ መልክተኛ ሙሐመድና እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፡፡ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትኾን በፊቶቻቸው ላይ ናት፡፡ ይህ በተውራት (የተነገረው) ጠባያቸው ነው፡፡ በኢንጂልም ውስጥ ምሳሌያቸው ቀንዘሉን አንደአወጣ አዝመራና፣ (ቀንዘሉ) እንዳበረታው፣ እንደወፈረምና፣ ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ኾኖ በአገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደ ቆመ (አዝመራ) ነው፡፡ (ያበረታቸውና ያበዛቸው) ከሓዲዎችን በእነርሱ ሊያስቆጭ ነው፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን የሠሩትን ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን ተስፋ አድርጎላቸዋል፡፡