caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Fath፣ አንቀጽ 11

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 111 · 48:11

سَيَقُولُ لَكَ ٱلْمُخَلَّفُونَ مِنَ ٱلْأَعْرَابِ شَغَلَتْنَآ أَمْوَٰلُنَا وَأَهْلُونَا فَٱسْتَغْفِرْ لَنَا يَقُولُونَ بِأَلْسِنَتِهِم مَّا لَيْسَ فِى قُلُوبِهِمْ قُلْ فَمَن يَمْلِكُ لَكُم مِّنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا إِنْ أَرَادَ بِكُمْ ضَرًّا أَوْ أَرَادَ بِكُمْ نَفْعًۢا بَلْ كَانَ ٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًۢا

Amharic Translation - Africa Academy11. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ከዐረብ ዘላኖች መካከል እነዚያ ከዘመቻ ወደ ኋላ የቀሩት «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸግረዉን ስለነበር ነውና (የቀረነው) ምህረትን ለምንልን» ይሉሃል:: በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ:: «አላህ እናንተን መጉዳትም ሆነ መጥቀም ቢፈልግ ከአላህ ለእናተ አንዳችን ለመከላከል የሚችል ማን ነው? በእውነቱ አላህ ለምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው።» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከአዕራብ ሰዎች እነዚያ (ከዘመቻ) ወደ ኋላ የቀሩት ለአንተ «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸገሩን፤ ስለዚህ ምሕረትን ለምንልን፤» ይሉሃል፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ፡፡ (አላህ) «በእናንተ ላይ ጉዳትን ቢሻ ወይም በእናንተ መጥቀምን ቢሻ ከአላህ (ለማገድ) ለእናንተ አንዳችን የሚችል ማነው? በእውነቱ አላህ፤በምትሠሰሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70