وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَوْ نَرَىٰ رَبَّنَا لَقَدِ ٱسْتَكْبَرُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ وَعَتَوْ عُتُوًّا كَبِيرًا
Amharic Translation - Africa Academy21. እነዚያ መገናኘታችንን የማይጠብቁ ሰዎች «በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም ወይም ጌታችንን ለምን አናይም?» አሉ። በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ። ታላቅንም አመጽ አመጹ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያም መገናኘታችንን የማይፈሩት በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም፡፡ ወይም ጌታችንን ለምን አናይም አሉ፡ በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ፡፡ ታላቅንም አመጽ አመፁ፡፡