caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Tahrim፣ አንቀጽ 8

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 107 · 66:8

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ تُوبُوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ تَوْبَةً نَّصُوحًا عَسَىٰ رَبُّكُمْ أَن يُكَفِّرَ عَنكُمْ سَيِّـَٔاتِكُمْ وَيُدْخِلَكُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ يَوْمَ لَا يُخْزِى ٱللَّهُ ٱلنَّبِىَّ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ نُورُهُمْ يَسْعَىٰ بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَٰنِهِمْ يَقُولُونَ رَبَّنَآ أَتْمِمْ لَنَا نُورَنَا وَٱغْفِرْ لَنَآ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Amharic Translation - Africa Academy8. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህ ነብዩን እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያመኑትን በማያሳፍርበት፤ ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲሆን፡- «ጌታችን ሆይ! ብርሃናችንን ሙላልን፤ ለእኛ ምህረትንም አድርግልን፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና» በሚሉበት ቀን ጌታችሁ ከናንተ ኃጢአቶቻችሁን ሊሰርዝላችሁ፤ ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶችም ሊያስገባችሁ ይከጅላልና ንጹህ የሆነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ንጹሕ የኾነችን ጸጸት በመጸጸት ወደ አላህ ተመለሱ፡፡ ጌታችሁ ከእናንተ ኀጢኣቶቻችሁን ሊሰርይላችሁ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውንም ገነቶች ሊያስገባችሁ ይከጀላልና፡፡ አላህ ነቢዩን፣ እነዚያንም ከእርሱ ጋር ያመኑትን በማያሳፍርበት ቀን ብርሃናቸው በፊቶቻቸውና በቀኞቻቸው የሚሮጥ ሲኾን «ጌታችን ሆይ! ብርሃናችንን ሙላልን፣ ለእኛ ምሕረትም አድርግልን፣ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና» ይላሉ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70