caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Talaaq الطلاق

12 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 99

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ إِذَا طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ فَطَلِّقُوهُنَّ لِعِدَّتِهِنَّ وَأَحْصُوا۟ ٱلْعِدَّةَ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ رَبَّكُمْ لَا تُخْرِجُوهُنَّ مِنۢ بُيُوتِهِنَّ وَلَا يَخْرُجْنَ إِلَّآ أَن يَأْتِينَ بِفَٰحِشَةٍ مُّبَيِّنَةٍ وَتِلْكَ حُدُودُ ٱللَّهِ وَمَن يَتَعَدَّ حُدُودَ ٱللَّهِ فَقَدْ ظَلَمَ نَفْسَهُۥ لَا تَدْرِى لَعَلَّ ٱللَّهَ يُحْدِثُ بَعْدَ ذَٰلِكَ أَمْرًا

Amharic Translation - Africa Academy1. አንተ ነብይ ሆይ! ሴቶችን መፍታት ባሰባችሁ ጊዜ፤ ለዒዳቸው ፍቷቸው፤ ዒዳንም ቁጠሩ፤ ጌታችሁን አላህን ፍሩ፤ ግልጽ የሆነችን ጠያፍ ካልሰሩ በስተቀር ከቤቶቻቸው አታውጧቸው:: አይውጡም፤ ይህችም የአላህ ህግጋት ናት:: የአላህንም ህግጋት የተላለፈ ሰው በእርግጥ ነፍሱን በደለ፤ ከዚህ (ፍች) በኋላ አላህ (የመማለስ) ነገርን ምናልባት ያመጣ እንደኾነ አታውቅም፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَإِذَا بَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ فَارِقُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ وَأَشْهِدُوا۟ ذَوَىْ عَدْلٍ مِّنكُمْ وَأَقِيمُوا۟ ٱلشَّهَٰدَةَ لِلَّهِ ذَٰلِكُمْ يُوعَظُ بِهِۦ مَن كَانَ يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجْعَل لَّهُۥ مَخْرَجًا

Amharic Translation - Africa Academy2. ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዟቸው፤ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፤ ከናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፤ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፤ ይሃችሁ በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُۥٓ إِنَّ ٱللَّهَ بَٰلِغُ أَمْرِهِۦ قَدْ جَعَلَ ٱللَّهُ لِكُلِّ شَىْءٍ قَدْرًا

Amharic Translation - Africa Academy3. ከማያስበዉም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል፤ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው:: አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው:: አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَٱلَّٰٓـِٔى يَئِسْنَ مِنَ ٱلْمَحِيضِ مِن نِّسَآئِكُمْ إِنِ ٱرْتَبْتُمْ فَعِدَّتُهُنَّ ثَلَٰثَةُ أَشْهُرٍ وَٱلَّٰٓـِٔى لَمْ يَحِضْنَ وَأُو۟لَٰتُ ٱلْأَحْمَالِ أَجَلُهُنَّ أَن يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجْعَل لَّهُۥ مِنْ أَمْرِهِۦ يُسْرًا

Amharic Translation - Africa Academy4. እነዚያም ከሴቶቻችሁ ከአደፍ (ከወር አበባ) ያቋረጡት በዒዳቸው ህግ ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሶስት ወር ነው:: እነዚያም ገና አደፍን ያላዩ ሴቶችም ዒዳቸው እንደዚሁ ነው:: የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለእርሱ መግራትን ያደርግለታል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يُكَفِّرْ عَنْهُ سَيِّـَٔاتِهِۦ وَيُعْظِمْ لَهُۥٓ أَجْرًا

Amharic Translation - Africa Academy5. ይህ የአላህ ፍርድ ነው:: ወደ እናንተ አወረደው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ሁሉ ኃጢአቶችን ከርሱ ይሰርዝለታል:: ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَسْكِنُوهُنَّ مِنْ حَيْثُ سَكَنتُم مِّن وُجْدِكُمْ وَلَا تُضَآرُّوهُنَّ لِتُضَيِّقُوا۟ عَلَيْهِنَّ وَإِن كُنَّ أُو۟لَٰتِ حَمْلٍ فَأَنفِقُوا۟ عَلَيْهِنَّ حَتَّىٰ يَضَعْنَ حَمْلَهُنَّ فَإِنْ أَرْضَعْنَ لَكُمْ فَـَٔاتُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ وَأْتَمِرُوا۟ بَيْنَكُم بِمَعْرُوفٍ وَإِن تَعَاسَرْتُمْ فَسَتُرْضِعُ لَهُۥٓ أُخْرَىٰ

Amharic Translation - Africa Academy6. ከችሎታችሁ ከተቀመጣችሁበት ስፍራ አስቀምጧቸው:: በእነርሱም ላይ ልታጣብቡ አትጉዷቸው:: የእርግዝና ባለቤቶችም ቢሆኑ እርጉዛቸውን እስኪወልዱ ድረስ በእነርሱ ላይ ቀልቡ። ለእናንተም ልጆቻችሁን ቢያጠቡላችሁ የልፋት ዋጋቸውን ስጧቸው:: በመካከላችሁም በመልካም ነገር ተመካከሩ፤ ብትቸጋገሩም ለእርሱ ሌላ (ሴት) ታጠባለታለች::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

لِيُنفِقْ ذُو سَعَةٍ مِّن سَعَتِهِۦ وَمَن قُدِرَ عَلَيْهِ رِزْقُهُۥ فَلْيُنفِقْ مِمَّآ ءَاتَىٰهُ ٱللَّهُ لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفْسًا إِلَّا مَآ ءَاتَىٰهَا سَيَجْعَلُ ٱللَّهُ بَعْدَ عُسْرٍ يُسْرًا

Amharic Translation - Africa Academy7. የችሎታ ባለቤት በችሎታው ልክ ይቀልብ፤ በእርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበበት ሰው አላህ ከሰጠው ይስጥ ነፍስን የሰጣትን ያህል እንጂ አያስገድድም:: አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَكَأَيِّن مِّن قَرْيَةٍ عَتَتْ عَنْ أَمْرِ رَبِّهَا وَرُسُلِهِۦ فَحَاسَبْنَٰهَا حِسَابًا شَدِيدًا وَعَذَّبْنَٰهَا عَذَابًا نُّكْرًا

Amharic Translation - Africa Academy8. ከከተማም መካከል ከጌታቸው እና ከመልዕክተኞች ትዕዛዝ ያመጹ በመሆናቸው፤ ብርቱን ቁጥጥር የተቆጣጠርናቸዉና መጥፎንም ቅጣት የቀጣናቸው ብዙ ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

فَذَاقَتْ وَبَالَ أَمْرِهَا وَكَانَ عَٰقِبَةُ أَمْرِهَا خُسْرًا

Amharic Translation - Africa Academy9. የነገራቸዉንም ቅጣት ቀመሱ:: የነገራቸዉም መጨረሻ ኪሳራ ሆነ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

أَعَدَّ ٱللَّهُ لَهُمْ عَذَابًا شَدِيدًا فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ يَٰٓأُو۟لِى ٱلْأَلْبَٰبِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ قَدْ أَنزَلَ ٱللَّهُ إِلَيْكُمْ ذِكْرًا

Amharic Translation - Africa Academy10. አላህ ለእነርሱ ብርቱ ቅጣትን አዘጋጀ:: እናንተም በአላህ ያመናችሁ የአእምሮ ባለ ቤቶች ሆይ! አላህን ፍሩ፤ አላህ ወደ እናንተ ግሳጼን በእርግጥ አወረደ፤

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

رَّسُولًا يَتْلُوا۟ عَلَيْكُمْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ مُبَيِّنَٰتٍ لِّيُخْرِجَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَمَن يُؤْمِنۢ بِٱللَّهِ وَيَعْمَلْ صَٰلِحًا يُدْخِلْهُ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا قَدْ أَحْسَنَ ٱللَّهُ لَهُۥ رِزْقًا

Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲኾኑ በእናንተ ላይ የሚያነብላችሁን መልዕክተኛን ላከ:: በአላህም አናቅጽ የሚያምን መልካምን ስራ የሚሰራም ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያገባዋል አላህ ለርሱ ሲሳይን በእርግጥ አሳመረ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ سَبْعَ سَمَٰوَٰتٍ وَمِنَ ٱلْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ ٱلْأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ ٱللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَىْءٍ عِلْمًۢا

Amharic Translation - Africa Academy12. አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው:: ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሮአል)፤ በመካከላቸዉም ትዕዛዙ ይወርዳል:: አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አላህም በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70