caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ At-Talaaq፣ አንቀጽ 11

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 99 · 65:11

رَّسُولًا يَتْلُوا۟ عَلَيْكُمْ ءَايَٰتِ ٱللَّهِ مُبَيِّنَٰتٍ لِّيُخْرِجَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ مِنَ ٱلظُّلُمَٰتِ إِلَى ٱلنُّورِ وَمَن يُؤْمِنۢ بِٱللَّهِ وَيَعْمَلْ صَٰلِحًا يُدْخِلْهُ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَآ أَبَدًا قَدْ أَحْسَنَ ٱللَّهُ لَهُۥ رِزْقًا

Amharic Translation - Africa Academy11. እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሰሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲኾኑ በእናንተ ላይ የሚያነብላችሁን መልዕክተኛን ላከ:: በአላህም አናቅጽ የሚያምን መልካምን ስራ የሚሰራም ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያገባዋል አላህ ለርሱ ሲሳይን በእርግጥ አሳመረ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣ ዘንድ የአላህን አንቀጾች ገላጮች ሲኾኑ በእናንተ ላይ የሚያነብላችሁን መልክተኛን (ላከ)፡፡ በአላህም የሚያምን፣ መልካምን ሥራ የሚሠራም ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባዋል፡፡ አላህ ለእርሱ ሲሳይን በእርግጥ አሳመረ፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70