فَإِذَا بَلَغْنَ أَجَلَهُنَّ فَأَمْسِكُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ أَوْ فَارِقُوهُنَّ بِمَعْرُوفٍ وَأَشْهِدُوا۟ ذَوَىْ عَدْلٍ مِّنكُمْ وَأَقِيمُوا۟ ٱلشَّهَٰدَةَ لِلَّهِ ذَٰلِكُمْ يُوعَظُ بِهِۦ مَن كَانَ يُؤْمِنُ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ وَمَن يَتَّقِ ٱللَّهَ يَجْعَل لَّهُۥ مَخْرَجًا
Amharic Translation - Africa Academy2. ጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዟቸው፤ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፤ ከናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፤ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፤ ይሃችሁ በአላህና በመጨረሻ ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqጊዜያቸውንም ለመዳረስ በተቃረቡ ጊዜ በመልካም ያዙዋቸው፡፡ ወይም በመልካም ተለያዩዋቸው፡፡ ከእናንተም ውስጥ ሁለት የትክክለኛነት ባለቤቶችን አስመስክሩ፡፡ ምስክርነትንም ለአላህ አስተካክሉ፡፡ ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የኾነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰጽበታል፡፡ አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡