caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ As-Saff الصف

14 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 109

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ سَبَّحَ لِلَّهِ مَا فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy1. በሰማያትና በምድር ውስጥ ያሉ ሁሉ አላህን አጠሩ:: እርሱ አሸናፊና ጥበበኛው ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy2. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ታወራላችሁ?

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

كَبُرَ مَقْتًا عِندَ ٱللَّهِ أَن تَقُولُوا۟ مَا لَا تَفْعَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. የማትሰሩትን ነገር መናገራችሁ በአላህ ዘንድ በመጠላት እጅግ ከበደ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلَّذِينَ يُقَٰتِلُونَ فِى سَبِيلِهِۦ صَفًّا كَأَنَّهُم بُنْيَٰنٌ مَّرْصُوصٌ

Amharic Translation - Africa Academy4. አላህ እነዚያን ልክ እንደተለሰነ ግንብ የተሰለፉ ሆነው በሃይማኖቱ የሚፋለሙትን ይወዳል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦ يَٰقَوْمِ لِمَ تُؤْذُونَنِى وَقَد تَّعْلَمُونَ أَنِّى رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيْكُمْ فَلَمَّا زَاغُوٓا۟ أَزَاغَ ٱللَّهُ قُلُوبَهُمْ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْفَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳም ለህዝቦቹ፡- «ህዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ የአላህ መልዕክተኛ መሆኔን እያወቃችሁ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ከእውነት በተዘነበሉ ጊዜ አላህም ልቦቻቸውን አዘነበለባቸው:: አላህ አመጸኞችን ህዝቦች አያቀናምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذْ قَالَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ يَٰبَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ إِنِّى رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَىَّ مِنَ ٱلتَّوْرَىٰةِ وَمُبَشِّرًۢا بِرَسُولٍ يَأْتِى مِنۢ بَعْدِى ٱسْمُهُۥٓ أَحْمَدُ فَلَمَّا جَآءَهُم بِٱلْبَيِّنَٰتِ قَالُوا۟ هَٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ

Amharic Translation - Africa Academy6. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የኢስራኢል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊት ያለውን የማረጋግጥና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልዕክተኛ ስሙ አህመድ በሆነውም የማበስር ስሆን ወደ እናንተ የተላኩ የአላህ መልዕክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ግልጽ ታዐምራቶችን ባመጣላቸው ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ ٱفْتَرَىٰ عَلَى ٱللَّهِ ٱلْكَذِبَ وَهُوَ يُدْعَىٰٓ إِلَى ٱلْإِسْلَٰمِ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلظَّٰلِمِينَ

Amharic Translation - Africa Academy7. እርሱ ወደ ኢስላም የሚጠራ ሲሆን በአላህ ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ይበልጥ በደለኛ ማን ነው? አላህ በዳዮችን ህዝቦች አይመራም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يُرِيدُونَ لِيُطْفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفْوَٰهِهِمْ وَٱللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَٰفِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy8. የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ:: ከሓዲያን ቢጠሉም እንኳ አላህ ብርሀኑን ገላጭ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy9. አላህ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልዕክተኛውን በመምሪያ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት (በኢስላም) ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው፡፡

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَىٰ تِجَٰرَةٍ تُنجِيكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ

Amharic Translation - Africa Academy10. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአሳማሚ ቅጣት የሚያድናችሁን ትርፋማ ንግድ ላመላክታችሁን?» በላቸው።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

تُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦ وَتُجَٰهِدُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ بِأَمْوَٰلِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ ذَٰلِكُمْ خَيْرٌ لَّكُمْ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. እርሱም በአላህና በመልዕክተኛው ታምናላችሁ:: በአላህ መንገድ በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ትታገላለችሁ:: ይህ ተግባር የምታውቁ ከሆናችሁ ለእናንተ የተሻለ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ وَيُدْخِلْكُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ وَمَسَٰكِنَ طَيِّبَةً فِى جَنَّٰتِ عَدْنٍ ذَٰلِكَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ

Amharic Translation - Africa Academy12. ኃጢአቶቻችሁን ይምራል:: ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸዉም ገነቶች ያስገባችኋል:: በመኖሪያ ገነቶችም በሚያምሩ ቤቶች ውስጥ ያስቀምጣችኋል:: ይህ ታላቅ እድል ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأُخْرَىٰ تُحِبُّونَهَا نَصْرٌ مِّنَ ٱللَّهِ وَفَتْحٌ قَرِيبٌ وَبَشِّرِ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy13. ሌላይቱንም የምትወዷትን ጸጋ ይሰጣችኋል:: እርሷም ከአላህ የሆነ እርዳታና ቅርብ የሆነ አገር መክፈት ነው:: አማኞችንም አብስር::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُونُوٓا۟ أَنصَارَ ٱللَّهِ كَمَا قَالَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ لِلْحَوَارِيِّـۧنَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ فَـَٔامَنَت طَّآئِفَةٌ مِّنۢ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَكَفَرَت طَّآئِفَةٌ فَأَيَّدْنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ عَلَىٰ عَدُوِّهِمْ فَأَصْبَحُوا۟ ظَٰهِرِينَ

Amharic Translation - Africa Academy14. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የመርየም ልጅ ዒሳ ለሐዋሪያቱ፡- «ወደ አላህ ረዳቴ ማን ነው» እንዳለና ሐዋርያቶቹም፡- «እኛ የአላህ ረዳት ነን» እንዳሉት ሁሉ እናንተም የአላህ ረዳቶች ሁኑ፤ ከኢስራኢል ልጆችም አንደኛዋ ቡድን አመነች:: ሌላይቱም ቡድን ካደች:: እነዚያን ያመኑትንም በጠላታቸው ላይ አበረታናቸው:: ከዚያ እነርሱም አሸናፊዎች ሆኑ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70