يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُونُوٓا۟ أَنصَارَ ٱللَّهِ كَمَا قَالَ عِيسَى ٱبْنُ مَرْيَمَ لِلْحَوَارِيِّـۧنَ مَنْ أَنصَارِىٓ إِلَى ٱللَّهِ قَالَ ٱلْحَوَارِيُّونَ نَحْنُ أَنصَارُ ٱللَّهِ فَـَٔامَنَت طَّآئِفَةٌ مِّنۢ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ وَكَفَرَت طَّآئِفَةٌ فَأَيَّدْنَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ عَلَىٰ عَدُوِّهِمْ فَأَصْبَحُوا۟ ظَٰهِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy14. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የመርየም ልጅ ዒሳ ለሐዋሪያቱ፡- «ወደ አላህ ረዳቴ ማን ነው» እንዳለና ሐዋርያቶቹም፡- «እኛ የአላህ ረዳት ነን» እንዳሉት ሁሉ እናንተም የአላህ ረዳቶች ሁኑ፤ ከኢስራኢል ልጆችም አንደኛዋ ቡድን አመነች:: ሌላይቱም ቡድን ካደች:: እነዚያን ያመኑትንም በጠላታቸው ላይ አበረታናቸው:: ከዚያ እነርሱም አሸናፊዎች ሆኑ::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! የመርየም ልጅ ዒሳ ለሐዋርያቶቹ «ወደ አላህ ረዳቴ ማነው?» እንዳለ ሐወርያቶቹም «እኛ የአላህ ረዳቶች ነን» እንዳሉት የአላህ ረዳቶች ኹኑ፡፡ ከእስራኤልም ልጆች አንደኛዋ ጭፍራ አመነች፡፡ ሌላይቱም ጭፍራ ካደች፡፡ እነዚያን ያመኑትንም በጠላታቸው ላይ አበረታናቸው፤ አሸናፊዎችም ኾኑ፡፡