وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِۦ يَٰقَوْمِ لِمَ تُؤْذُونَنِى وَقَد تَّعْلَمُونَ أَنِّى رَسُولُ ٱللَّهِ إِلَيْكُمْ فَلَمَّا زَاغُوٓا۟ أَزَاغَ ٱللَّهُ قُلُوبَهُمْ وَٱللَّهُ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْفَٰسِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy5. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) ሙሳም ለህዝቦቹ፡- «ህዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደ እናንተ የአላህ መልዕክተኛ መሆኔን እያወቃችሁ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?» ባለ ጊዜ የሆነውን አስታውስ:: ከእውነት በተዘነበሉ ጊዜ አላህም ልቦቻቸውን አዘነበለባቸው:: አላህ አመጸኞችን ህዝቦች አያቀናምና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqሙሳም ለሕዝቦቹ «ሕዝቦቼ ሆይ! እኔ ወደእናንተ የአላህ መልክተኛ መኾኔን በእርግጥ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን ታሰቃዩኛላችሁ?» ባለ ጊዜ (አስታውስ፡፡ ከእውነት) በተዘነበሉም ጊዜ አላህ ልቦቻቸውን አዘነበላቸው፡፡ አላህም አመጸኞችን ሕዝቦች አያቀናም፡፡