caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Munaafiqoon المنافقون

11 አንቀጾች · መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 104

بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِذَا جَآءَكَ ٱلْمُنَٰفِقُونَ قَالُوا۟ نَشْهَدُ إِنَّكَ لَرَسُولُ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ إِنَّكَ لَرَسُولُهُۥ وَٱللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ لَكَٰذِبُونَ

Amharic Translation - Africa Academy1. አስመሳዮች በመጡህ (ወደ አንተ በመጡ) ጊዜ «አንተ የአላህ መልዕክተኛ መሆንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን» ይላሉ:: አላህም አንተ በእርግጥ መልዕክተኛው መሆንህን ያውቃል:: አላህም አስመሳዮችን ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ٱتَّخَذُوٓا۟ أَيْمَٰنَهُمْ جُنَّةً فَصَدُّوا۟ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ إِنَّهُمْ سَآءَ مَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy2. መሓላዎቻቸውን ጋሻ አድርገው ያዙ:: ከአላህም መንገድ ከለከሉ:: እነርሱ ይሰሩት የነበሩት ነገር ሁሉ ከፋ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ ءَامَنُوا۟ ثُمَّ كَفَرُوا۟ فَطُبِعَ عَلَىٰ قُلُوبِهِمْ فَهُمْ لَا يَفْقَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy3. ይህ እነርሱ (በምላስ) አምነው ከዚያም (በልብ) የካዱ በመሆናቸው በልቦቻቸዉም ላይ ታተመባቸው:: ስለዚህ እነርሱ አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا رَأَيْتَهُمْ تُعْجِبُكَ أَجْسَامُهُمْ وَإِن يَقُولُوا۟ تَسْمَعْ لِقَوْلِهِمْ كَأَنَّهُمْ خُشُبٌ مُّسَنَّدَةٌ يَحْسَبُونَ كُلَّ صَيْحَةٍ عَلَيْهِمْ هُمُ ٱلْعَدُوُّ فَٱحْذَرْهُمْ قَٰتَلَهُمُ ٱللَّهُ أَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ

Amharic Translation - Africa Academy4. ባየሃቸው ጊዜ አካሎቻቸው ያስደንቁሃል:: ቢናገሩም ንግግራቸውን ታዳምጣለህ:: እነርሱ ልክ ወደ ግድግዳ የተጠጉ ግንዶችን ይመስላሉ:: ጩኸትን ሁሉ በእነርሱ ላይ ነው ብለው ያስባሉ:: እነርሱ ጠላቶች ናቸውና ተጠንቀቃቸው:: አላህ ይጋደላቸው:: (ከእምነት) እንዴት ይመለሳሉ (ያፈገፍጋሉ)::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ تَعَالَوْا۟ يَسْتَغْفِرْ لَكُمْ رَسُولُ ٱللَّهِ لَوَّوْا۟ رُءُوسَهُمْ وَرَأَيْتَهُمْ يَصُدُّونَ وَهُم مُّسْتَكْبِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy5. ለእነርሱም፡- «ኑ የአላህ መልዕክተኛ ለእናንተ ምህረትን ይለምንላችኋል» በተባሉ ጊዜ በማፌዝ ራሶቻቸውን ያዞራሉ:: እነርሱም ትዕቢተኞች ሆነው ሲሸሹ ታያቸዋለህ::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

سَوَآءٌ عَلَيْهِمْ أَسْتَغْفَرْتَ لَهُمْ أَمْ لَمْ تَسْتَغْفِرْ لَهُمْ لَن يَغْفِرَ ٱللَّهُ لَهُمْ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى ٱلْقَوْمَ ٱلْفَٰسِقِينَ

Amharic Translation - Africa Academy6. ምህረትን ብትለምንላቸውም ባትለምንላቸዉም በእነርሱ ላይ ሁሉም እኩል ነው:: አላህ ለእነርሱ በፍጹም አይምርም:: አላህ አመጸኛ ህዝቦችን አይመራምና::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

هُمُ ٱلَّذِينَ يَقُولُونَ لَا تُنفِقُوا۟ عَلَىٰ مَنْ عِندَ رَسُولِ ٱللَّهِ حَتَّىٰ يَنفَضُّوا۟ وَلِلَّهِ خَزَآئِنُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَلَٰكِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ لَا يَفْقَهُونَ

Amharic Translation - Africa Academy7. እነርሱ፡- «እነዚያ ከአላህ መልዕክተኛ ዘንድ ያሉት ሰዎች እስከ ሚበታተኑ ድረስ ምጽዋት አትስጡ» የሚሉ ናቸው:: የሰማያትና የምድር ድልቦች የአላህ ብቻ ናቸው:: ግን አስመሳዮች አይገነዘቡም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَقُولُونَ لَئِن رَّجَعْنَآ إِلَى ٱلْمَدِينَةِ لَيُخْرِجَنَّ ٱلْأَعَزُّ مِنْهَا ٱلْأَذَلَّ وَلِلَّهِ ٱلْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِۦ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَٰكِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ

Amharic Translation - Africa Academy8. «ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከእርሷ ያስወጣል» ይላሉ:: አሸናፊነትም ለአላህ ለመልዕክተኛው እና ለምዕምና ብቻ ነው:: ግን አስመሳዮች አያውቁም::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَٰلُكُمْ وَلَآ أَوْلَٰدُكُمْ عَن ذِكْرِ ٱللَّهِ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُو۟لَٰٓئِكَ هُمُ ٱلْخَٰسِرُونَ

Amharic Translation - Africa Academy9. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያታልሏችሁ (አያዘናጓችሁ):: ይህንንም የሚሰሩ ሰዎች እነዚያ እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَأَنفِقُوا۟ مِن مَّا رَزَقْنَٰكُم مِّن قَبْلِ أَن يَأْتِىَ أَحَدَكُمُ ٱلْمَوْتُ فَيَقُولَ رَبِّ لَوْلَآ أَخَّرْتَنِىٓ إِلَىٰٓ أَجَلٍ قَرِيبٍ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ ٱلصَّٰلِحِينَ

Amharic Translation - Africa Academy10. አንዳችሁም ሞት ሳይመጣበትና «ጌታየ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎችም ሰዎች እንድሆን ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ» ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

وَلَن يُؤَخِّرَ ٱللَّهُ نَفْسًا إِذَا جَآءَ أَجَلُهَا وَٱللَّهُ خَبِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy11. ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣባት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም:: አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ አዋቂ ነው::

የዚህን አንቀጽ ሁሉንም ትርጉሞች ይመልከቱ →

ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70