بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ إِذَا جَآءَكَ ٱلْمُنَٰفِقُونَ قَالُوا۟ نَشْهَدُ إِنَّكَ لَرَسُولُ ٱللَّهِ وَٱللَّهُ يَعْلَمُ إِنَّكَ لَرَسُولُهُۥ وَٱللَّهُ يَشْهَدُ إِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ لَكَٰذِبُونَ
Amharic Translation - Africa Academy1. አስመሳዮች በመጡህ (ወደ አንተ በመጡ) ጊዜ «አንተ የአላህ መልዕክተኛ መሆንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን» ይላሉ:: አላህም አንተ በእርግጥ መልዕክተኛው መሆንህን ያውቃል:: አላህም አስመሳዮችን ውሸታሞች መሆናቸውን ይመሰክራል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqመናፍቃን በመጡህ ጊዜ «አንተ የአላህ መልክተኛ መኾንህን በእርግጥ (ምለን) እንመሰክራለን» ይላሉ፡፡ አላህም አንተ በእርግጥ መልክተኛው መኾንህን ያውቃል፡፡ አላህም መናፍቃን (ከልብ እንመሰክራለን በማለታቸው) ውሸታሞች መኾናቸውን ይመሰክራል፡፡