caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 151

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:151

قُلْ تَعَالَوْا۟ أَتْلُ مَا حَرَّمَ رَبُّكُمْ عَلَيْكُمْ أَلَّا تُشْرِكُوا۟ بِهِۦ شَيْـًٔا وَبِٱلْوَٰلِدَيْنِ إِحْسَٰنًا وَلَا تَقْتُلُوٓا۟ أَوْلَٰدَكُم مِّنْ إِمْلَٰقٍ نَّحْنُ نَرْزُقُكُمْ وَإِيَّاهُمْ وَلَا تَقْرَبُوا۟ ٱلْفَوَٰحِشَ مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ وَلَا تَقْتُلُوا۟ ٱلنَّفْسَ ٱلَّتِى حَرَّمَ ٱللَّهُ إِلَّا بِٱلْحَقِّ ذَٰلِكُمْ وَصَّىٰكُم بِهِۦ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy151. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) በላቸውም: «ኑ ጌታችሁ በእናተ ላይ እርም ያደረገውን ነገርና (በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ። እርሱም በአላህ ምንንም ነገር አታጋሩ:: ለወላጆቻችሁም በጎ ስራን ስሩ:: ልጆቻችሁንም ድህነትን ፈርታችሁ አትግደሉ:: እኛ እናንተንም ሆነ እነርሱን እንመግባችኋለንና:: ወደ ግልፅም ይሁን ድብቅ መጥፎ ስራ አትቅረቡ:: ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሀቅ ቢሆን እንጂ አትግደሉ:: ይሀችሁ! ታውቁ ዘንድ በእርሱ አዘዛችሁ።
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ኑ፤ ጌታችሁ በእናንተ ላይ እርም ያደርገውን ነገር (በእርሱም ያዘዛችሁን) ላንብብላችሁ» በላቸው፡፡ «በእርሱ (በአላህ) ምንንም ነገር አታጋሩ፡፡ ለወላጆችም በጎን ሥራ (ሥሩ)፡፡ ልጆቻችሁንም ከድህንት (ፍራቻ) አትግደሉ፡፡ እኛ እናንተንም እነርሱንም እንመግባችኋለንና፡፡ መጥፎ ሥራዎችንም ከእርሷ የተገለጸውንም የተደበቀውንም ሁሉ አትቅረቡ፡፡ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ በሕግ ቢኾን እንጅ አትግደሉ፡፡ ይህን ታውቁ ዘንድ (አላህ) በእርሱ አዘዛችሁ፡፡»
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70