قُلْ هَلُمَّ شُهَدَآءَكُمُ ٱلَّذِينَ يَشْهَدُونَ أَنَّ ٱللَّهَ حَرَّمَ هَٰذَا فَإِن شَهِدُوا۟ فَلَا تَشْهَدْ مَعَهُمْ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا وَٱلَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِٱلْـَٔاخِرَةِ وَهُم بِرَبِّهِمْ يَعْدِلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy150. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «እነዚያ አላህ ይህንን እርም ማድረጉን የሚመሰክሩትን ምስክሮቻችሁን እስቲ አምጡ።» በላቸው:: ቢመሰክሩም ከእነርሱ ጋር አትመስክር:: የእነዚያን በአናቅጻችን ያስተባበሉትን፤ የእነዚያንም በጌታቸው ሌላን የሚያስተካክሉ ሲሆኑ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑትን ሰዎች ዝንባሌዎች አትከተል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«እነዚያን አላህ ይህን እርም ማድረጉን የሚመሰክሩትን ምስክሮቻችሁን አምጡ» በላቸው፡፡ ቢመሰክሩም ከእነርሱ ጋር አትመስክር፡፡ የነዚያንም በአንቀጾቻችን ያስተባበሉትን የነዚያንም እነርሱ በጌታቸው (ሌላን) የሚያስተካክሉ ሲኾኑ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑትን ሰዎች ዝንባሌዎች አትከተል፡፡